Loading
ያለ ፡ አማጭ ፡ ታስፈልገኛለህ (፬x) መተኪያ ፡ የሌለህ (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ በድስታዬ ፡ በሃዘኔም ፡ ብበለፅግ ፡ ብደኸይም ታስፈልገኛለህ (፪x) በጥጋቤ ፡ በረሃቤም ፡ በጤናዬም ፡ በህመሜም ታስፈልገኛለህ (፪x) ማንም (፫x) ፡ አይተካህም ምንም (፫x) ፡ አይተካህም በጉብዝናዬ ፡ በድካሜም ፡ ሲሳካልኝ ፡ ሳስይካም ታስፈልገኛለህ (፪x) በእርካታዬም ፡ በጥማቴም ፡ በአደባባይ ፡ በጓዳዬም ታስፈልገኛለህ (፪x) ማንም (፫x) ፡ አይተካህም ምንም (፫x) ፡ አይተካህም ለጠቢቡ ፡ ለአዋቂዉም ፡ ለታናሹ ፡ ለታላቁም ታስፈልገኛለህ (፪x) ለታጀበው ፡ ለብቸኛውም ፡ ለእርሱሙ ፡ ሰው ፡ ለንጉሡም ታስፈልገኛለህ (፪x) ማንም (፫x) ፡ አይተካህም ምንም (፫x) ፡ አይተካህም የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ነህ (፪x) የሕይወት ፡ እንጀራ ፡ የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ነህ የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ነህ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.