Loading
የከበበኝ ፡ የደገፈኝ ፡ አሃሃ የቀደመኝ ፡ የተከተለኝ (፪x) አምላኬ ፡ ነው ፡ የሚያኖረኝ (፮x) እግዚአብሔር ፡ ነው የጓደኛዬ ፡ ነገር ፡ የአየሩ ፡ ሁኔታ የዘመን ፡ ወጣ ፡ ውረድ ፡ የጠላት ፡ ድንፋታ አይደለም ፡ ሚዛኔ ፡ ነገን ፡ የምለካበት ቃልኪዳን ፡ ይዣለው ፡ እምነቴን ፡ የምጥልበት እርሱ ፡ አይለወጥም ፡ አምላኬ ፡ አይለወጥም እግዚአብሔር ፡ አይለወጥም ስለዚህ ፡ እኔ ፡ አልጠፋም (፫x) የከበበኝ ፡ የደገፈኝ ፡ አሃሃ የቀደመኝ ፡ የተከተለኝ (፪x) አምላኬ ፡ ነው ፡ የሚያኖረኝ (፮x) እግዚአብሔር ፡ ነው የጨባጭ ፡ መረጃ ፡ ቢያቀብለኝ ፡ ኖሮዬ እኔም ፡ መረጃ ፡ አለኝ ፡ ቃል ፡ ሰጥቶኛል ፡ ጌታዬ እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ አቤነዘር ፡ ብያለሁ ትናንት ፡ የረዳኝን ፡ ነገም ፡ እታመነዋለሁ እርሱ ፡ አይለወጥም ፡ አምላኬ ፡ አይለወጥም እግዚአብሔር ፡ አይለወጥም ስለዚህ ፡ እኔ ፡ አልጠፋም (፫x) የክብር ፡ አምላክ ፡ የክብር አብሮኝ ፡ ሆነና ፡ እግዚአብሔር ያስጨነቀኝ ፡ አዋረዳቸው እንደ ፡ መንገድ ፡ ጭቃ ፡ ረገጣቸው የክበር ፡ ንጉሥ ፡ የክብር ቀድሞኝ ፡ ወጣና ፡ እግዚአብሔር ጠላቶቼን ፡ ሁሉ ፡ አወካቸው እንደ ፡ ትብያ ፡ እንደ ፡ እብቅ ፡ በተናቸው እርሱ ፡ አይለወጥም ፡ አምላኬ ፡ አይለወጥም እግዚአብሔር ፡ አይለወጥም ስለዚህ ፡ እኔ ፡ አልጠፋም (፫x) መብልና ፡ መጠጥ ፡ የድንኳኔ ፡ ውበት መቀበሪያ ፡ ሥፍራ ፡ የአሟሟቴም ፡ ዓይነት አይደለም ፡ ጭንቀቴ ፡ እኔን ፡ የሚያሳስበኝ ከዚህ ፡ የሚሻገር ፡ የደመቀ ፡ ተስፋ ፡ አለኝ እርሱ ፡ አይለወጥም ፡ አምላኬ ፡ አይለወጥም እግዚአብሔር ፡ አይለወጥም ስለዚህ ፡ እኔ ፡ አልጠፋም (፫x) የከበበኝ ፡ የደገፈኝ ፡ አሃሃ የቀደመኝ ፡ የተከተለኝ (፪x) አምላኬ ፡ ነው ፡ የሚያኖረኝ (፮x) እግዚአብሔር ፡ ነው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.