Loading
እግዚአብሔር ፡ በይሁዳ ፡ የታወቅህ ድንኳንህ ፡ በሳሌም ፡ ማደሪያህ ፡ በጽዮን አንተ ፡ ብርሃን ፡ ተላብሰህ ፡ ደምቀህ ግርማዊነትህ ፡ ከዘለዓለም ፡ ተራሮች ፡ ሁሉ ፡ ይልቃል ልበ ፡ ሙሉ ፡ የሆኑት ፡ ሁሉ ፡ አለቁ ከተግጻጽህ ፡ የተነሳ ፡ ፈረስና ፡ ፈረሰኛው ጭልጥ ፡ ድብን ፡ ብለው ፡ ተኙ የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ ሆይ በአንተ ፡ ፊት ፡ ማንስ ፡ መቆም ፡ ይችላል (፪x) መፈራት ፡ ያለብህ ፡ አንተ ፡ ብቻ መወደስ ፡ ያለብህ ፡ አንተ ፡ ብቻ እልሃለው ፡ ዛሬም ፡ እኔም ፡ ቆሜ አንተው ፡ በሰጠኸኝ ፡ ዘመንና ፡ ቅኔ ልዑል ፡ ሆይ ፡ ማደሪያህ ፡ ይባረክ ቅዱስ ፡ ሥምህ ፡ ይባረክ ልዑል ፡ ሆይ ፡ ማደሪያህ ፡ ይባረክ (፬x) ከኃያላኑ ፡ በፊት ፡ ኃያል ከብርቱዎቹ ፡ በፊት ፡ ብርቱ የነበርህ አንተ ፡ ነህ ፡ የምትኖር አንተ ፡ ነህ ፡ ፈጣሪያቸው አንተ ፡ ነህ ፡ ገዢያቸው አንተ ፡ ነህ እግዚአብሔር አንተ ፡ ነህ ፣ አንተ ፡ ነህ እነዚያ ፡ ዘመናቸው ፡ አልቆ ፡ ተረቱ እንደ ፡ ቀልድ ፡ አባሩ ፡ አለፉ ፡ ተረሱ ሲራቡ ፡ ሌላ: ነገን: ማየት ባሉበት ፡ መዘግየት ፡ ከመሞት ፡ መሰንበት አልቻሉም ፡ አልቻሉም አለመሞት ፡ አልቻሉም ነገን ፡ ማየት ፡ አልቻሉም አልቻሉም ፡ አልቻሉም ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ሳይ ፡ አፈሩን አልኩኝ ፡ አወይ ፡ አቤት ፡ አቤት ስንት ፡ ጀግና ፡ ስንት ፡ ጐበዝ ስንት ፡ አይደፈር ፡ ኖሯል ፡ በታች ከምረግጠው ፡ መሬት አሻቅቤ ፡ ሳይ ፡ ወደላይ ፡ ወደላይኛው ፡ ሠማይ አየሁ ፡ የዘመን ፡ ልክ ፡ የዘመን ፡ ቁጥር የዘመኑ ፡ ባለቤት ፡ የቁጥሩም ፡ ባለቤት የሁሉን ፡ በላይ ፡ ሞትን ፡ የማያይ መወደስ ፡ ያለበት ፡ እርሱ ፡ ብቻ መመለክ ፡ ያለበት ፡ እርሱ ፡ ብቻ እልሃለው ፡ እኔም ፡ ዛሬም ፡ እኔም ፡ ቆሜ አንተው ፡ በሰጠኸኝ ፡ ዘመንና ፡ ቅኔ ልዑል ፡ ሆይ ፡ ማደሪያህ ፡ ይባረክ ቅዱስ ፡ ሥምህ ፡ ይባረክ ማደሪያህ ፡ ይባረክ ልዑል ፡ ሆይ ፡ ተባረክ ዘለዓለምም ፡ ቢሆን ፡ የእርሱ ፡ ልክ ፡ አይደለም መች ፡ በዚህ ፡ ይለካል ፡ የሠማይ ፡ የምድሩ ፡ የሁሉ ፡ ፈጣሪ ኧረ ፡ እርሱ ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ ዘለዓለምን ፡ ፈጥሮ ፡ ወዶ ፡ በፈቃዱ ዘለዓለምን ፡ ዘለዓለም ፡ ያኖረዋል ፡ እንጂ ጭራሽ ፡ አይለካም ፡ እግዜሩ ፡ ክብሩ ፡ አይመዘንም ክብሩ ፡ ለብቻው ፡ ነው ፡ ዝናው ፡ ለብቻው ፡ ነው እስኪ ፡ አለው: ይበለኝ ፡ አንድ ፡ ሥጋ ፡ ለባሽ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ እስኪ ፡ የትኛው ፡ ነው የዘለዓለም ፡ ነዋሪ ፡ የዘለዓለም ፡ ፈጣሪ የሁሉ ፡ በላይ ፡ ሞትን ፡ የማያዪ መወደስ ፡ ያለበት ፡ እርሱ ፡ ብቻ መከበር ፡ ያለበት ፡ እርሱ ፡ ብቻ እልሃለው ፡ እኔም ፡ ዛሬም ፡ እኔም ፡ ቆሜ አንተው ፡ በሰጠኸኝ ፡ ዘመንና ፡ ቅኔ ልዑል ፡ ሆይ ፡ ማደሪያህ ፡ ይባረክ ቅዱስ ፡ ሥምህ ፡ ይባረክ ልዑል ፡ ሆይ ፡ ተባረክ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.