Loading
አልተረሳሁም ባንተ ዘንድ ከቶ አተወኝም ከመንገድ የሁልጊዜ ነው ወዳድነትህ አትለወጥም ሁኔታን አይተህ አልተረሳሁም ባንተ ዘንድ ከቶ አተወኝም ከመንገድ የሁልጊዜ ነው ወዳድነትህ አትለወጥም ሁኔታን አይተህ ታውቀኛለህ አንተ በስሜ ከቶ አተወኝም አትረሳኝም አንተ ሰውን ከቶ አትጥልም በዚህ እፅናናለሁ አንተን አይሀለሁ በዚህ እፅናናለሁ እበረታለሁ አንተን ብቻ አይሀለሁ ኢየሱስ... የልቤ ጌታ ውስጤን አዋቂ ኢየሱስ... ባገኘኝ ሁሉ ልቤን ጠባቂ ተስፋዬ አንተ ብቻ ነህ የልቤ ብርታት የመኖር አቅሜ የልቤ ጠገን የልቤ ፅናት የለኝም የምመካበት -ልቤን የማስጠጋበት የውስጤን አንተ ታውቃለህ-ልቤን ትደግፋለህ የለኝም የምፅናናበት- ልቤን የምጥልበት የውስጤን አንተ ታያለህ ልቤን ትደግፋለህ ኢየሱስ... ያልተፈጠሩ ቀኖቼን ያየህ ኢየሱስ... ያሰፈርካቸው በክብር ፅፈህ አምናለሁ ለኔም እንዲህ ነህ አትዘነጋኝም በእጆችህ መዳፍ የቀረፅከኝን አትረሳኝም ከመዳፍህ ካልጠፋሁ ካወቅከኝ ይበቃኛል የተረሳሁ ሲመስለኝ መንፈስህ ያፀናኛል ከአይኖችህ ፊት ውላለሁ እንደብዙ ሆናለሁ ታውቀኛለህ በስሜ ሁሉን ባንተ እረሳለሁ እፅናናለሁ ፊትህን ሳይ እበረታለሁ ፊትህን ሳይ ቀና እላለሁ ፊትህን ሳይ እበረታለሁ አይንህን ሳይ የለኝም የምመካበት -ልቤን የማስጠጋበት የውስጤን አንተ ታውቃለህ-ልቤን ትደግፋለህ የለኝም የምፅናናበት- ልቤን የምጥልበት የውስጤን አንተ ታያለህ ልቤን ትደግፋለህ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.