Loading
ለተቀበሉት : ለዚህ : አደራ በእምነት : ቆሙ : እስከመጨረሻ ሐዋርያቱ : ያለፉበት : ለወንጌሉ : ነው : የተሰዉት በአሰቃቂ : ሞት : አለፈ : ሕይወታቸው እልፍ : ምስክር : አይኑ : እያያቸው ለአደራቸው : ነው : የጨከኑት : ላመኑበት እየተበሉ : እየተሰቃዩ : የወንጌሉን : አደራ : ለእኛ : አቆዩ(x2) ነገ : እንዳይነሳ : እግዚአብሔርን : የማያውቅ : ትውልድ ማነው : ሕዝቡን : የሚመራው : ምሳሌ : እየሆነ ወደ : አምላኩ : መንገድ (x2) አለ : ምስክር : አለ : መሬቱ ጻድቃን : ስለወንጌል : የተሰዉበት በተራቡ : አንበሶች : እየተበሉ የወንጌልን : አደራ : ለእኛ : አቆዩ በሮም : ሜዳ : ላይ : ፈስሷል : ደማቸው እልፍ : ምስክር : አይኑ : እያያቸው ለአደራቸው : ነው : የጨከኑት : ለአመኑበት እየተበሉ : እየተሰቃዩ : የወንጌልን : አደራ : ለእኛ : አቆዩ(x2) ነገ : እንዳይነሳ : እግዚአብሔርን : የማያውቅ : ትውልድ ማነው : ሕዝቡን : የሚመራው : ምሳሌ : እየሆነ ወደ : አምላኩ : መንገድ በአፄ : ዘረያዕቆብ : የተሰዉት ለወንጌሉ : ነው : ጸንተው : የቆሙት ከነነፍሳቸው : እየተቀበሩ : የወንጌልን : አደራ : ለእኛ : አቆዩ በስደት : ዘመን : በአብዮቱ : ስያንገላቷቸው : በየእሥር : ቤቱ ጨከኑ : ለእምነት : ለሃይማኖታቸው : ለተቀበሉት : ለአደራቸው ነገ : እንዳይነሳ : እግዚአብሔርን : የማያውቅ : ትውልድ ማነው : ሕዝቡን : የሚመራው : ምሳሌ : እየሆነ ወደ : አምላኩ : መንገድ እናንተ : ቅዱሳኖች : ያቆያችሁልኝ : የወንጌል : አደራ እንዴት : ልሸከመው : እንዴት እንዴት : ነው :?? : (እጅግ : ይከብዳልና)x2 የነገውን : ትውልድ : በእጄ : ላይ : ይኸውና ዛሬ : ይውረድብኝ : እናንተን : የረዳው የእግዚአብሔር : ፀጋ(x2)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.