Loading
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ ብደጋግም የማይሰለቸኝ ፡ ሁሌ ፡ ብዘምር አሁንም ፡ መልሼ ፡ ብደጋግም የማይሰለቸኝ ፡ ሁሌ ፡ ብዘምር የመዳኔ ፡ ነገር ቀሎ ፡ ስለመጣ ፡ አይቀልም ፡ በሕይወቴ ፡ የመስቀሉ ፡ ስራ በክብር ፡ ታጅቦ ፡ ይመጣል ፡ ሊወስደኝ ፡ አርጐኛል ፡ ሙሽራ ሰማይ ፡ ደስታ ፡ ሆነ ፡ ዕልልታው ፡ ቀለጠ ፡ በእኔ ፡ መዳን እንዴት ፡ መታደል ፡ ነው ፡ በበጉ ፡ ዙፋን ፡ ፊት ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መሆን አጋንንት ፡ ቢወጣ ፡ ሽባ ፡ ቢተረተር የሞተ ፡ ቢነሳ ፡ ይህም ፡ ያልፋል ፡ ምድር አይወዳደርም ፡ ይሄኛው ፡ ተአምር የመዳኔ ፡ ነገር ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ ብደጋግም የማይሰለቸኝ ፡ ሁሌ ፡ ብዘምር አሁንም ፡ መልሼ ፡ ብደጋግም የማይሰለቸኝ ፡ ሁሌ ፡ ብዘምር የመዳኔ ፡ ነገር አማኝ ፡ ሞት ፡ አይፈራ ፡ እንግዳ ፡ ነውና ፡ በዚህ ፡ ምድር ፡ ላይ ይናፍቃል ፡ እንጂ ፡ ከአምላኩ ፡ ጋር ፡ መኖር ፡ በላይ ፡ በሰማይ ሰው ፡ ዓለምን ፡ ቢያተርፍ ፡ ነፍሱን ፡ ግን ፡ ቢያጐድል ፡ መቼ ፡ ይጠቅመዋል ከክርስቶስ ፡ ጋራ ፡ ለዘላለም ፡ መኖር ፡ ከሁሉም ፡ ይበልጣል ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማ ፡ ሞኝህን ፡ አስፈራራ ሞት ፡ አይፈራም ፡ አማኝ ፡ ሰማይ ፡ የእርሱ ፡ ስፍራ ይሄ ፡ አለኝ ፡ ብዬ ፡ ቁሳቁስ ፡ አልቆጥር የእኔ ፡ ፡ ሃብት ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ሞትን ፡ የሚሻገር የመዳኔ ፡ ነገር ክብር ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል ዝና ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል ጉልበት ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል ሃዘን ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል ማግኘት ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል ማጣት ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል የማያልፈው ፡ አንድ ፡ ነገር በሰማያት ፡ ያለ ፡ ክብር ተጽፎልኝ ፡ ስሜ ፡ በላይ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ደስታ ፡ አለ ፡ ወይ በዚህ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ደስታ ሞልቶኛል ፡ ዕልልታ ለዚህ ፡ ነው ፡ ጩኸቴ ሰማይ ፡ ቤት ፡ በመግባቴ ክብር ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል ዝና ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል ጉልበት ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል ሃዘን ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል ማግኘት ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል ማጣት ፡ ቢሆን ፡ ያልፋል የማያልፈው ፡ አንድ ፡ ነገር በሰማያት ፡ ያለ ፡ ክብር ተጽፎልኝ ፡ ስሜ ፡ በላይ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ደስታ ፡ አለ ፡ ወይ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.