Loading
አንዴ ፡ በፍቅሩ ፡ ልቤ ፡ ተነክቶ ሌላውን ፡ ናቀው ፡ በኢየሱስ ፡ ረክቶ በነገረኝ ፡ ቃል ፡ በእርሱ ፡ ጸንቼ ዘና ፡ ብያለሁ ፡ ጌታን ፡ ሰምቼ ፡ (፫ ፡ ጊዜ) ተረጋግቷል ፡ ልቤ ፡ ተረጋግቷል ተረጋግቷል ፡ ልቤ ፡ ተረጋግቷል በአምላኩ ፡ ታምኖ ፡ እፎይ ፡ አለ ከአንተ ፡ ድምጽ ፡ ውጪ ፡ አልሰማ ፡ አለ ኢየሱስን ፡ ይዞ ፡ ቃሉን ፡ ተመርኩዞ በትከሻው ፡ መሃል ፡ ተንተርሶ ኢየሱስን ፡ ይዞ ፡ ቃሉን ፡ ተመርኩዞ በትከሻው ፡ መሃል ፡ ተንተርሶ ልቤም ፡ አይፈራም ፡ ሁኔታን ፡ አይቶ አይደነብርም ፡ ጠላቱን ፡ ሰምቶ እነደ ፡ አንበሳ ፡ ነው ፡ ውስጤ ፡ ድፍረቴ አንዴ ፡ አትርፌያለሁ ፡ በማንነቴ በወይኑ ፡ ሃረግ ፡ ፍሬ ፡ ባይገኝ ቢሆንም ፡ ባይሆን ፡ አያስጨንቀኝ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ዓይናወጥም ፡ ከቶ ፡ እምነቴ የሰላም ፡ አምላክ ፡ ገብቷል ፡ ከቤቴ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ይህን ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ጀግና ፡ ሚሉት አይደነብርም ፡ በሚነግሩት በሰልፍ ፡ መሃል ፡ በምጥ ፡ ተይዞ ይደረድራል ፡ በገናን ፡ ይዞ ክበር ፡ እያለ ፡ ንገሥ ፡ እያለ ክበር ፡ እያለ ፡ ንገሥ ፡ እያለ ተረጋግቷል ፡ ልቤ ፡ ተረጋግቷል ተረጋግቷል ፡ ልቤ ፡ ተረጋግቷል በአምላኩ ፡ ታምኖ ፡ እፎይ ፡ አለ ከአንተ ፡ ድምጽ ፡ ውጪ ፡ አልሰማ ፡ አለ ኢየሱስን ፡ ይዞ ፡ ቃሉን ፡ ተመርኩዞ በትከሻው ፡ መሃል ፡ ተንተርሶ ኢየሱስን ፡ ይዞ ፡ ቃሉን ፡ ተመርኩዞ በትከሻው ፡ መሃል ፡ ተንተርሶ ጠላት ፡ ሁኔታን ፡ እያሳየኝ ልቤ ፡ እንዲከፋ ፡ ሲጠብቀኝ ይናፍቀዋል ፡ እንባ ፡ ከዓይኖቼ ምሥጋና ፡ ሞልቷል ፡ ከከንፈሮቼ በወይኑ ፡ ሃረግ ፡ ፍሬ ፡ ባይገኝ ቢሆንም ፡ ባይሆን ፡ አያስጨንቀኝ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ዓይናወጥም ፡ ከቶ ፡ እምነቴ የሰላም ፡ አምላክ ፡ ገብቷል ፡ ከቤቴ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ይህን ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ጀግና ፡ ሚሉት አይደነብርም ፡ በሚነግሩት በሰልፍ ፡ መሃል ፡ በምጥ ፡ ተይዞ ይደረድራል ፡ በገናን ፡ ይዞ ክበር ፡ እያለ ፡ ንገሥ ፡ እያለ ክበር ፡ እያለ ፡ ንገሥ ፡ እያለ የእምነት ፡ አባቶቼ ፡ እንዲህ ፡ መከሩኝ ሁል ፡ ጊዜ ፡ በጌታ ፡ ተደሰት ፡ አሉኝ ወህኒ ፡ ቢከቷቸው ፡ የማይመች ፡ ቦታ መዘመር ፡ ቀጠሉ ፡ ውስጣቸው ፡ ነው ፡ ደስታ ቢሆንም ፡ ባይሆን ፡ አመስግኑ መልካም ፡ እንዲሆን ፡ አመስግኑ ዕልል ፡ በሉ ፡ አመስግኑ ዕልል ፡ በሉ ፡ እንጂ ፡ አመስግኑ አታጉረምርሙ ፡ አመስግኑ አምላክ ፡ አትሙ ፡ አመስግኑ ዕልል ፡ በሉ ፡ አመስግኑ ዕልል ፡ በሉ ፡ እንጂ ፡ አመስግኑ ቅዱሳን ፡ ሁሉ ለእርሱ ፡ ዘምሩ አንሱ ፡ በገና አምጡ ፡ ምሥጋና ቢሆንም ፡ ባይሆን ፡ አመስግኑ መልካም ፡ እንዲሆን ፡ አመስግኑ ዕልል ፡ በሉ ፡ አመስግኑ ዕልል ፡ በሉ ፡ እንጂ ፡ አመስግኑ አታጉረምርሙ ፡ አመስግኑ አምላክ ፡ አትሙ ፡ አመስግኑ ዕልል ፡ በሉ ፡ አመስግኑ ዕልል ፡ በሉ ፡ እንጂ ፡ አመስግኑ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.