Loading
ስፈራ ፡ ስቸር ፡ ማልተነፍሰው ፡ ሚስጥሬ ፡ በዝቷል እኔ ፡ ባልናገር ፡ የልብ ፡ ወዳጄ ፡ የውስጤን ፡ ያውቃል እርሱ ፡ እንደሚያውቀኝ ፡ ሰው ፡ አያውቀኝም ፡ እንጂ መቆም ፡ አልችልም ፡ እንኳን ፡ በንጉሥ ፡ በራሴም ፡ ደጅ የምህረት ፡ ዓይኑ ፡ ዛሬም ፡ ያየኛል አልሰለቸኝም ፡ ይፈልገኛል (፪x) ፈላጊዬ ፡ መሃሪዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ወዳጄ አይዞሽ ፡ የሚለኝ ፡ እኔን ፡ ሚያበረታኝ ነው ፡ የልብ ፡ ወዳጄ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ እንዳትወደኝ ፡ በመልካምነቴ ይህ ፡ አይደለም ፡ ማንነቴ እንዳትጠላኝ ፡ ደግሞ ፡ በጥፋቴ ፍቅር ፡ ነህ ፡ አያስችልህም ፡ አባቴ ያለ ፡ ምክንያት ፡ ወደህ ፡ በምክንያት ፡ አትጠላም ለምህረትህ ፡ ስፍር ፡ መለኪያ ፡ የለውም የአንተ ፡ ፍቅር ፡ መነሺያው ፡ ከራስህ የመውደድ ፡ ልብ ፡ የማያልቅብህ (፪x) የእኔ ፡ ጌታ ከወዳጅ ፡ ከፍቶ ፡ ልጅህ ፡ ድርሻዬን ፡ ብሎ ፡ እርም ፡ እንዳላለ አልመች ፡ ቢለው ፡ የሸፈተበት ፡ አባቴን ፡ አለ አባትነቱን ፡ የበደል ፡ ብዛት ፡ መች ፡ ይሽረዋል ሁልን ፡ እረስቶ ፡ ደግሞ ፡ እንደገና ፡ ልጄ ፡ ይለዋል በምህረት ፡ ዓይኑ ፡ ዛሬም ፡ ያየኛል አልሰለቸኝም ፡ ይፈልገኛል የምህረት ፡ ዓይኑ ፡ ዛሬም ፡ ያየኛል አልሰለቸኝም ፡ ይፈልገኛል ፈላጊዬ ፡ መሃሪዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ወዳጄ አይዞሽ ፡ የሚለኝ ፡ እኔን ፡ ሚያበረታኝ ነው ፡ የልብ ፡ ወአጄ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.