Loading
ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ኃያል ፡ ሥም ፡ አለው በዚህ ፡ ሥም ፡ አምነን ፡ ድነናል ፡ ይኸው ምስክሮቹ ፡ ነን ፡ ሕይወት ፡ ደርሶናል ሰማይ ፡ ሲጎበኘን ፡ ለዓለም ፡ በርተናል ተጠቅልለናል ፡ በክርስቶስ ፡ በኃያሉ ፡ ሥም ከነበርንበት ፡ ዓለም ፡ የለንም የሚበልጥ ፡ አይተን ፡ የሚደንቅ ፡ ክብር ሰውን ፡ ኑ ፡ እንላለን ፡ አልፈን ፡ ከምድር አምላክ ፡ ሥጋ ፡ ሆነ ፡ ለእኛ ፡ ማለደ ከአብ ፡ አስታረቀን ፡ ስርየት ፡ ወረደ ሕያው ፡ ልጆቹ ፡ ነን ፡ ዳግም ፡ ወልዶናል ዘላለም ፡ ሲያገኘን ፡ ከሞት ፡ ጠፍተናል ተጠቅልለናል ፡ በክርስቶስ ፡ በኃያሉ ፡ ሥም ከነበርንበት ፡ ዓለም ፡ የለንም የሚበልጥ ፡ አይተን ፡ የሚደንቅ ፡ ክብር ሰውን ፡ ኑ ፡ እንላለን ፡ አልፈን ፡ ከምድር እናንት ፡ መኳንንቶች ፡ በሩን ፡ ክፈቱ የክብር ፡ ንጉሥ ፡ ይግባ ፡ በሩን ፡ ክፈቱ ይሄ ፡ ንጉሥ ፡ ማነው ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው የክብር ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) እርሱ ፡ እግዚአብሔር የክብር ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ የክብር ፡ ሁሉ ፡ ገዢ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብርቱና ፡ ኃያል (፪x) የሰማይ ፡ የምድሩ ፡ የልዑላን ፡ ጌታ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብርቱና ፡ ኃያል (፪x) ሆሆ ፡ ኃያሉ ፡ እግዚአብሔር እርሱ ፡ እኛን ፡ ጎበኘ እንድንዘምርለት ፡ ዙሪያው ፡ ሰበሰበን ሆሆ ፡ እግዚአብሔር ፡ ረዳን እግዚአብሔር ፡ አሰበን በየደረስንበት ፡ ኃያል ፡ መዝሙር ፡ ሆነን ምሥጋና ፡ የተገባው ፡ እርሱ ፡ ነው ውዳሴ ፡ የተገባው ፡ እርሱ ፡ ነው ለእኛ ፡ ታየን ፡ መድኃኔዓለም እንደርሱ ፡ የለም ፡ ዘላለም ለእኛ ፡ ተገለጠ ፡ መድኃኔዓለም እንደርሱ ፡ የለም ፡ ዘላለም ዝማሬ ፡ የተገባው ፡ እርሱ ፡ ነው ስግደትም ፡ የተገባው ፡ እርሱ ፡ ነው ለእኛ ፡ ታየን ፡ መድኃኔዓለም እንደርሱ ፡ የለም ፡ ዘላለም ለእኛ ፡ ተገለጠ ፡ መድኃኒዓለም እንደሱ ፡ የለም ፡ ዘላለም
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.