Loading
ጌታ ፡ ነው ፡ ቢጎድልም ፡ ቢሞላ በሕይወቴ ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ ሌላ ችግሩ ፡ ከቦ ፡ ቢያስጨንቀኝ ከርስቴ ፡ ማን ፡ ሊነቀንቀኝ እኔ ፡ አለሁ (፪x) አልነሳም ፡ ከመሰዊያው (፪x) ጌታ ፡ ነው ፡ ቢጎድልም ፡ ቢሞላ በህይወቴ ፡ የለም ፡ ከሱ ፡ ሌላ ችግሩ ፡ ከቦ ፡ ቢያስጨንቀኝ ከርስቴ ፡ ማን ፡ ሊነቀንቀኝ እኔ ፡ አለሁ (፪x) አልነሳም ፡ ከመሰዊያው (፪x) እየተፀለየ ፡ እየተዘመረ ከቀደመው ፡ ይልቅ ፡ ችግሩ ፡ ጨመረ ሰባት ፡ እጥፍ ፡ ቢሆን ፡ ጨምሮ ፡ ጨምሮ እግዚአብሔር ፡ ያድናል ፡ ችግርን ፡ ሰባባሮ እየተፀለየ ፡ እየተዘመረ ከቀደመው ፡ ይልቅ ፡ እሳቱ ፡ ጨመረ ሰባት ፡ እጥፍ ፡ ቢነድ ፡ ጨምሮ ፡ ጨምሮ እግዚአብሔር ፡ ያድናል ፡ የእሳትን ፡ ኃይል ፡ ሰብሮ ያድናል ፡ ዛሬም/እኮ ፡ ያድናል ለጌታ ፡ ምን ፡ ይሳነዋል ሕያው ፡ ነው ፡ አልተለወጠም ያድናል ፡ ለዘላለም (፪x) የሰጠ ፡ እርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ቢነሳ ፡ ከልካይስ ፡ አለው ፡ ወይ አትበይ ፡ እንደሰነፎች ከሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የሚመች እኔ ፡ አለሁ (፪x) አልነሳም ፡ ከመሰዊያው (፪x) እንዲህ ፡ ነው ፡ አይባል ፡ የጌታ ፡ አሰራሩ (፪x) ፈፅሞ ፡ አይታማም ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ በምክሩ (፪x) ቢዘገይም ፡ እንኳን ፡ በጊዜው ፡ ይደርሳል (፪x) ካለቀሰ ፡ ሁሉ ፡ እንባ ፡ ይታበሳል (፪x) ያድናል ፡ ዛሬም ፡ ያድናል ለጌታ ፡ ምን ፡ ይሳነዋል ሕያው ፡ ነው ፡ አልተለወጠም ያድናል ፡ ለዘላለም
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.