Loading
ጐበስ ፡ ቀና ፡ ብለህ ፡ ያኔ ፡ በአምሳልህ ፡ የፈጠርከው አልተገኘም ፡ በስፍራው ፡ ሆኖ ፡ አንተ ፡ እንዳስቀመጥከው በምኞት ፡ ተሳበ ፡ ወደቀ ፡ በጠላት ፡ ተረታ እራሱን ፡ በራሱ ፡ በደለ ፡ መቅሰፍትን ፡ አመጣ የተፍገመገመ ፡ እንዳይወድቅ ፡ መድኃኒት ፡ ላክለት እንደማይችል ፡ አውቅህ ፡ እንዲሁ ፡ ምህረት ፡ አድርግለት አዝ፦ በቃ ፡ በለው ፡ እስኪ ፡ ማረው እንዲህ ፡ ተቅበዝብዟል ፡ በአምሳልህ ፡ የፈጠርከው በቃ ፡ በለው ፡ እስኪ ፡ ማረው እንዲህ ፡ ተብቀንቅኗል ፡ በአምሳልህ ፡ የፈጠርከው ፍጥረት ፡ ተቀሰፈ ፡ አለቀ ፡ እንዲሁ ፡ በከንቱ እሮሮና ፡ ሃዘን ፡ ያሰማል ፡ ሁሉም ፡ በየቤቱ ልጆች ፡ አዋቂዎች ፡ ሳይባል ፡ አዛውንቶች ፡ ሁሉ ያለአጋዥ ፡ ያለጧሪ ፡ ቀርተው ፡ ጐዳናውን ፡ ሁሉ ፡ ሞሉ ተንከራታቹን ፡ ሰው ፡ አስበው ፡ ልቡን ፡ መልስለት ረሃብ ፡ ቸነፈር ፡ በሽታውን ፡ አንተ ፡ አስወግድለት አዝ፦ በቃ ፡ በለው ፡ እስኪ ፡ ማረው እንዲህ ፡ ተቅበዝብዟል ፡ በአምሳልህ ፡ የፈጠርከው በቃ ፡ በለው ፡ እስኪ ፡ ማረው እንዲህ ፡ ተብቀንቅኗል ፡ በአምሳልህ ፡ የፈጠርከው እረ ፡ ይቅር ፡ በለን ፡ ጩኸታችን ፡ ይውጣ የሚያግዝ ፡ የለም ፡ ወይ ፡ እንዲህ ፡ ስንቀጣ ወዴት ፡ አቤት ፡ እንበል ፡ ለማን ፡ እንንገረው ፍጥረት ፡ ተቅበዝብዟል ፡ አጋዥ ፡ እንደሌለው ከነገሥታት ፡ መፍትሄ ፡ ጠፍቷል ከጠቢባን ፡ ጥበብ ፡ ተሰውሯል አቅም ፡ ያለው ፡ ለውጥን ፡ የሚያመጣ አንድም ፡ የለም ፡ ሚያድነን ፡ ከቁጣ አንተ ፡ ግን ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነህና የሚሳንህ ፡ ምንም ፡ የለምና አግዘው ፡ እንጂ ፡ ተመልከተው ይሄ ፡ ፍጥረት ፡ ካለአንተ ፡ ማን ፡ አለው አዝ፦ በቃ ፡ በለው ፡ እስኪ ፡ ማረው እንዲህ ፡ ተቅበዝብዟል ፡ በአምሳልህ ፡ የፈጠርከው በቃ ፡ በለው ፡ እስኪ ፡ ማረው እንዲህ ፡ ተብቀንቅኗል ፡ በአምሳልህ ፡ የፈጠርከው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.