Loading
መውጣቴ ፡ መግባቴ ፡ በአንተ ፡ ተጠብቆ ከእኔ ፡ ጋር ፡ እንዳለህ ፡ ጠላቴ ፡ እንኳን ፡ አውቆ ይሸሸኝ ፡ ገመረ ፡ በሄድኩበት ፡ ስፍራ ሁሉን ፡ አስረገጥከኝ ፡ ሆነህ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ለአንተ ፡ ሲያንህ ፡ ነው (፬x) ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ ስምህን ፡ ልባርከው ያንን ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ ያለፍኩት ፡ በአንተ ፡ ነው እልፍ ፡ ቃል ፡ ቢነገር ፡ አይገልጥህምና መቅደስህ ፡ ገብቼ ፡ ልበል ፡ ጎንበስ ፡ ቀና (፪x) አዝ፦ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን አሳልፈኸኛል ፡ ያንን ፡ ክፉውን ፡ ቀን ሌላ ፡ ቃል ፡ የለኝም ፡ ልበልህ ፡ ተመስገን አሳልፈኸኛል ፡ ያንን ፡ ክፉውን ፡ ቀን ሌላ ፡ ቃል ፡ የለኝም ፡ ልበልህ ፡ ተመስገን (፪x) ምክንያት ፡ ፈልጌ ፡ ላመስግን ፡ እንጂ ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ልዘምር ፡ እንጂ ስላልጠፋሁኝ ፡ ዛሬም ፡ ከአንተ ፡ ደጅ (፬x) ምክንያት ፡ ፈልጌ ፡ ላመስግን ፡ እንጂ ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ልዘምር ፡ እንጂ ስላልጠፋሁኝ ፡ ዛሬም ፡ ከአንተ ፡ ደጅ (፯x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.