Loading
መከራን ፡ ባየሁበት ፡ ምድር በገፉኝ ፡ ሰዎች ፡ ልከበር ታሪኬን ፡ ከገለበጥከው ልቤን ፡ ደስ ፡ ካሰኘኸው ምሥጋናዬን ፡ ይኸው ፡ በፊትህ እንዳከበርከኝ ፡ ላከብርህ ያለኝም ፡ ይኸው ፡ ነውና አንተው ፡ ከሰጠኸኝ ፡ ሌላ ፡ አሃሃ አንተው ፡ ከሰጠኸኝ ፡ ሌላ አዝ፦ ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ተመስገን ተመስገን ፡ ተመስገን (፪x) በምሽት ፡ በሬ ፡ ሲንኳኳ መች ፡ መሰለኝ ፡ የምትመጣ ለካ ፡ ከሩቅ ፡ ተመልክተህ አስተዳዳሬ ፡ የአላማረህ አንተው ፡ ነህ ፡ የተጠጋኸኝ አስፈሪውን ፡ ሌት ፡ ያሳለፍከኝ ከብሬን ፡ ከደጄ ፡ አፍስሰህ ጠረኔን ፡ ለወጥክ ፡ አጣፍጠህ ፡ አህህ ጠረኔን ፡ ለወጥክ ፡ አጣፍጠህ አዝ፦ ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ተመስገን ተመስገን ፡ ተመስገን (፪x) ምሥጋናዬን ፡ ከወደድከው ስሰዋውም ፡ ካሸተትከው ከቃዬል ፡ መስዋዕት ፡ ካስበለጥከው ለአንተ ፡ ስሰዋ ፡ ውላለሁ ቀጥ ፡ ብሎ ፡ ወደላይ ፡ ይውጣ አርጐ ፡ በፊትህ ፡ ጌታ ደስ ፡ የሚያሰኝህ ፡ ምሥጋና ይሽተት ፡ ማደሪያህ ፡ ይግባና አሜን ፡ ይሽተት ፡ ማደሪያህ ፡ ይግባና አዝ፦ ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ተመስገን ተመስገን ፡ ተመስገን (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.