Loading
በእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ የሚመሩ ፡ እነዚህ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጆች ፡ ናቸው። ይላል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቃል። ታዲያ ፡ አንድ ፡ ማለዳ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ሳለሁኝ ጌታን ፡ በውስጤ ፡ የተሞሉትን ፡ ጥያቄዎች ፡ ለመጠየቅ እየተዘጋጀሁኝ ፡ እንደዚህ ፡ እያልኩት ፡ ነበረ። እነዚህን ፡ ጥያቄዎች ፡ በዝማሬ ፡ እነግራቹሃለሁ ፤ በመጀመሪያም ፡ እንደዚህ ፡ ስል ፡ ጠየኩት። አዝ፦ አባባ ፡ አባ ፡ አባባ (፪x) የልጅህን ፡ ጩኸት ፡ ስማ (፪x) ጌታም ፡ እንደዚህ ፡ ሲል ፡ በአባትነት ፡ ፍቅር ፡ ይናገረኝ ፡ ጀመረ ልጄ ፡ እኔም ፡ እሰማሃለሁ ሳትጠይቀኝ ፡ እረዳለሁ ብረሳህ ፡ ቀኜ ፡ ትርሳኝ ብተውህ ፡ አያስችለኝም አንዳንዴ ፡ ስለምንህ ፡ አትሰማኝም ስጠይቅህ ፡ ቶሎ ፡ አትሰጠኝም ለምንድነው ፡ አባ ፡ ምትከለክለኝ እጅህን ፡ ሰብስበህ ፡ ዝም ፡ የምትለኝ ጌታም ፡ እንደዚህ ፡ ሲል ፡ በሚያባብል ፡ ቃሎቹ ፡ ይናገረኝ ፡ ጀመረ ልጄ ፡ መች ፡ ሁሉ ፡ ይጠቅምሃል አንዳንዱ ፡ እኮ ፡ ይጐዳሃል አንተ ፡ ስለማታውቀው ፡ ነዉ መች ፡ መሰለህ ፡ አምሮህ ፡ ብታየው ስከለክልህ ፡ አይክፋህ አትፍጠን ፡ ቶሎ ፡ ለኩርፊያ ጠላት ፡ ይህንን ፡ አይቶ በኩርፊያህ ፡ ደስ ፡ አታሰኘው እንደሳሙኤል ፡ አባ ፡ እኔንም ፡ ጥራኝ ድምጽህን ፡ ለይተህ ፡ አሳውቀኝ የኤሊ ፡ ድምጽማ ፡ መቼ ፡ ይጠቅመኛል እንደራሱ ፡ ልጆች ፡ ያበላሸኛል አቤት ፡ ይሄ ፡ ጌታ ፡ በፍቅር ፡ መናገር ፡ ሲችል ፡ እንደዚህ ፡ ሲል ፡ ተናገረ ልጄ ፡ ለሰዎች ፡ ድምጽማ ፡ እኔ ፡ መች ፡ እተውሃለሁ እንደ ፡ መልካም ፡ እርሻ ፡ ሁሌ ፡ እኮተኩትሃለሁ የጽድቅ ፡ ቡካያዬ ፡ ነህ ፡ ፍሬህን ፡ አበዛዋለው ዘርህን ፡ እንደከዋክብት ፡ ምድርን ፡ እሞላታለሁ አዝ፦ አባባ ፡ አባ ፡ አባባ (፪x) የልጅህን ፡ ጩኸት ፡ ስማ (፪x) ጌታም ፡ እንደዚህ ፡ ሲል ፡ በአባትነት ፡ ፍቅር ፡ ይናገረኝ ፡ ጀመረ ልጄ ፡ እኔም ፡ እሰማሃለሁ ሳትጠይቀኝ ፡ እረዳለሁ ብረሳህ ፡ ቀኜ ፡ ትርሳኝ ብተውህ ፡ አያስችለኝም የኤልዛቤል ፡ ዛቻ ፡ አስፈርቶኝ ከክትክታው ፡ ዛፍ ፡ ስር ፡ ወድቂያለሁኝ ረሃቡ ፡ ጸንቶብኝ ፡ ቶሎ ፡ ሳይገድለኝ አባ ፡ በጊዜ ፡ ና ፡ ቶሎ ፡ መግበኝ ጌታም ፡ በፍቅር ፡ ቃሎቹ ፡ እየደጋገመ ፡ ይናገረኝ ፡ ቀጠለ ከሰማይ ፡ መልአኬን ፡ ልኬ ፡ ልጄ ፡ እኔ ፡ እመግብሃለሁ ሁሉ ፡ የሞላኝ ፡ አባትህ ፡ እኔ ፡ ለአንተ ፡ መቼ ፡ እሰጥህሃለሁ ዳቦ ፡ ስትለምነኝ ፡ ድንጋይ ፡ ዓሣ ስትለምን ፡ እባብን እኔ ፡ መች ፡ እሰጥሃለሁ ፡ ልጄ ፡ አንተን ፡ የሚጐዳህን ከእናቴ ፡ ማህፀን ፡ መርጠህ ፡ የለየኸኝ ሰልችተህ ፡ ጣል ፡ ጣል ፡ ተው ፡ አታድርገኝ አንተ ፡ የጣልከኝ ፡ እለት ፡ ጉዴ ፡ ይፈላል ያለ ፡ አንተስ ፡ እኔ ፡ መች ፡ ያምርብኛል የፍቅር ፡ ቃሎች ፡ የሞሉት ፡ ጌታ ፡ ደግሞ ፡ እንደዚህ ፡ ብሎ ፡ ተናገረኝ እናት ፡ እንኳ ፡ ልጇን ፡ ረስታ ምናልባት ፡ ትጥል ፡ ይሆናል ልጄ ፡ እኔ ፡ ግን ፡ አልረሳህም ያለ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ አይሆንልኝም እጅና ፡ እግሬ ፡ የቆሰለልህ የደሜ ፡ ካሳ ፡ የሆነህ ልጄ ፡ ልጥልህ ፡ ባስብም አንጀቴ ፡ እኮ ፡ አይችልልኝም አዝ፦ የምትወደኝ ፡ አባባ (፪x) ምሥጋናዬ ፡ ቤትክን ፡ ይሙላው ዕልልታዬ ፡ ቤትክን ፡ ይሙላው ምሥጋና ፡ ልቤን ፡ በሞላው ፡ ጊዜ ፡ ጌታም ፡ እንደዚህ ፡ እያለ ፡ መናገር ፡ ጀመረ ልጄ ፡ ፈጥኜ ፡ እመጣለሁ ከእኔ ፡ ጋር ፡ አኖርሃለሁ እምባ ፡ ያራሰው ፡ ፊትህን ያኔ ፡ እኔ ፡ አብሳለሁኝ አዝ፦ የምትወደኝ ፡ አባባ (፪x) ምሥጋናዬ ፡ ቤትክን ፡ ይሙላው ዕልልታዬ ፡ ቤትክን ፡ ይሙላው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.