Loading
መኖሪያዬ ፡ የዘላለም ፡ አምላክ የአባቶቼ ፡ የነ ፡ ሙሴ ፡ ኣባት እንደ ፡ እግዚኣብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም የሚያውቅልኝ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ አላገኝም ብታድነኝም ፡ ባታዳነኝም ፡ አንተ ፡ መልካም ፡ ነህ ይህንን ፡ አድርግ ፡ ያንን ፡ አታድርግ ፡ መች ፡ ትባላለህ ላደረራግህ ፡ ማስተካከያ ፡ ከማንም ፡ አትሻም ፍፁም ፡ በስራህ ፡ ፍፁም ፡ በምክርህ ፡ አትሳሳትም ያስጨነቀኝ ፡ ቀንበሬን ፡ ውስጤን ፡ አንቆ ፡ የያዘው ለእኔ ፡ እንጂ ፡ ቢከብደኝ ፡ ኢየሱሴ ፡ ለአንተ ፡ እንዴት ፡ እንዴት ፡ ቀላል ፡ ነው የዛሬው ፡ ድቅድቅ ፡ ሌሊቴ ፡ ይገባሃል ፡ ሚስጥሩ ፊትህን ፡ አያየሁ ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ አላለሁ ፡ ሰላም ፡ ነው አዝ፦ ሰላም ፡ ነው ፡ እላለሁ ፡ በእጅህ ፡ የገባውን ፡ ነገሬን ፡ እያየሁ ሰላም ፡ ነው ፡ እላለሁ ፡ ውስጤ ፡ ሸክም ፡ አዝሎ ፡ እጅህን ፡ አያየሁ አልገባሽ ፡ ቢለኝ ፡ ነገሩ ፡ ማዕበሉን ፡ ወጀቡን ፡ ፈርቼ ውስጤ ፡ ብርዱ ፡ ተሰማኝ ፡ ሰው ፡ ነኝና ፡ ሰግቼ ጉልበቴ ፡ እልሃለሁ ፡ ዛሬ ፡ አቅሜ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አቤቱ እምነቴ ፡ እንደው ፡ አልታመነም አይተኸኛል ፡ በብዙ ፡ ግን ፡ እላለሁ አዝ፦ ሰላም ፡ ነው ፡ እላለሁ ፡ ያደረክልኝ ፡ ትናንትን ፡ እያየሁ ሰላም ፡ ነው ፡ እላለሁ ፡ በዚህ ፡ ኣይቀጥልም ፡ ክብርህን ፡ አያለሁ ሰላም ፡ ነው ፡ እላለሁ ፡ ያደረክልኝ ፡ ትናንትን ፡ እያየሁ ሰላም ፡ ነው ፡ እላለሁ ፡ ይህም ፡ ሌሊት ፡ ያልፋል ፡ ክብርህን ፡ አያለሁ ደህና ፡ ነው ፡ ካለች ፡ ሱንማይቷ የአንድ ፡ ልጇን ፡ ነፍስ ፡ ኣጥታ ፡ ከቤቷ ታድያ ፡ እንዴት ፡ አልል ፡ ሰላም ፡ ነው ባለቤት ፡ አለኝ ፡ የኔ ፡ አይደለሁም በትንሽ ፡ ትልቁ ፡ ብዙ ፡ ጭንቀቴ መልስ ፡ እንዳይሆነኝ ፡ ለዘመመው ፡ ቤቴ ተረድቻለሁ ፡ ይህንን ፡ አውቄአለሁ ነገሬን ፡ ሁሉ ፡ አስረክቤዋለሁ መኖሪያዬ ፡ የዘላለም ፡ አምላክ ያባቶቼ ፡ የነ ፡ ሙሴ ፡ ኣባት እንደ ፡ እግዚኣብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም የሚያውቅልኝ ፡ አንደአንተ ፡ አላገኝም ብታድነኝም ፡ ባታዳነኝም ፡ አንተ ፡ መልካም ፡ ነህ ይህንን ፡ አድርግ ፡ ያንን ፡ አታድርግ ፡ መች ፡ ትባላለህ ላደረራግህ ፡ ማስተካከያ ፡ ከማንም ፡ ኣትሻም ፍፁም ፡ በሥራህ ፡ ፍፁም ፡ በምክርህ ፡ አትሳሳትም ሰላም ፡ ነው (፬x) ሰላም ፡ ነው (፬x) አውጃለሁ ፡ ዛሬም ፡ መልካምንትህን ፡ ባልሞላው ፡ ነገሬ ስንፍና ፡ አልሰብክም ፡ ዕምነቴን ፡ አልጥልም ፡ ከንቱ ፡ ተናገሬ ከአንተ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ ለመጪው ፡ ዘመኔ ፡ እኔ ፡ አላውቅምና መቆዘሜን ፡ ጥዬ ፡ ይህም ፡ ያልፋል ፡ ብዬ ፡ ልለፍ ፡ በምሥጋና ብርቱ ፡ ሰልፍ ፡ ሲሆን ፡ ሕይወቴ እንድማር ፡ ነው ፡ አባቴ ነፋሱ ፡ ሲያይል ፡ ሲበረታ ድንቅህን ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የማታ ፡ የማታ (፪x) ብርቱ ፡ ሰልፍ ፡ ሲሆን ፡ ህይወቴ ለትምህርቴ ፡ ነው ፡ አባቴ ወጀቡ ፡ ቢያይል ፡ ቢበረታ ግን ፡ ድሉ ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ የማታ ፡ የማታ (፪x) ሰላም ፡ ነው (፬x) ሰላም ፡ ነው (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.