Loading
የምፈልገውን ፡ ሁሉ ፡ ባገኝ የምፈልገው ፡ ደስታ ፡ ጋራ ፡ አልደርስም ስደርስበት ፡ ይቀልብኛል ሳልጠግበው ፡ ይሰለቸኛል የእኔ ፡ ክፍተት ፡ ሌላ ፡ ነው ብርም ፡ ወርቅም ፡ አይደለም ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ረሃቤ መንፈስ ፡ ነው ፡ ጥጋቤ በህልውናህ ፡ ሥር ፡ መሆን በአንተ ፡ መኖር ፡ ውሎ ፡ ማደር በመገኘትህ ፡ የታሰበ ፡ ሰዉ ምነኛ ፡ የታደለ ፡ ነው አስበኝ ፡ የእኔንም ፡ በህልውናህ በሚያጽናናው ፡ በመንፈስህ ይህ ፡ ነው ፡ ጥማቴ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ጉጉቴ ክብርህን ፡ ማየት ፡ ነው ፡ መሻቴ ትርጉም ፡ ለጠፋው ፡ ሕይወቴ ምላሽ ፡ ሲታጣ ፡ ከሞላው ፡ ቤቴ ለሞኖር ፡ ስዝል ፡ ሲደክመኝ ባዶነቴ ፡ ሲጮህብኝ የእኔ ፡ ክፍተት ፡ ሌላ ፡ ነው ያለኝ ፡ ነገር ፡ አይደለም ኢየሱስ ፡ ነህ ፡ ረሃቤ መንፈስው ፡ ነው ፡ ጥጋቤ በህልውናህ ፡ ሥር ፡ መሆን በአንተ ፡ መኖር ፡ ውሎ ፡ ማደር በመገኘትህ ፡ የታሰበ ፡ ሰዉ ምነኛ ፡ የታደለ ፡ ነው አስበኝ ፡ የእኔንም ፡ በህልውናህ በሚያጽናናው ፡ በመንፈስህ ይህ ፡ ነው ፡ ጥማቴ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ጉጉቴ ክብርህን ፡ ማየት ፡ ነው ፡ መሻቴ ህልሜ ፡ አንተን ፡ ማየት ፡ በኑሮዬ ህልሜ ፡ አንተን ፡ ማየት ፡ ነው ፡ ጉጉቴ የደስታዬ ፡ ልክ ፡ ሰላሜ ፡ እርካታዬ ጥግ ፡ ፍስሃዬ ፡ ኢየሱስ ይህ ፡ ነው ፡ ጥማቴ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ጉጉቴ ክብርህን ፡ ማየት ፡ ነው ፡ መሻቴ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.