Loading
ልጨምር ፡ እንጂ ፡ እኔም ፡ እንዲህ ፡ ልበል ሸክሜን ፡ ከላዬ ፡ ላረክለኝ ፡ ገለል ብዙ ፡ ብለውሃል ፡ ወዳጅ ፡ ጓደኞቼ አይበቃም ፡ ልጨምር ፡ እኔም ፡ ተስማምቼ መልካምነትህን ፡ ባለኝ ፡ አቅም ፡ ላውራ ተነግሮ ፡ ባያልቅም ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ ስራ አዝ፦ መልካም ፡ ነህ ፡ ከተባልከው ፡ በላይ (፪x) ስትሰራ ፡ የሌለብህ ፡ ከልካይ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሁልጊዜ ፡ ኤልሻዳይ መልካም ፡ ነህ ፡ ከተባልከው ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ በላይ መልካም ፡ ነህ ፡ ከተባልከው ፡ በላይ ስትሰራ ፡ የሌለብህ ፡ ከልካይ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሁልጊዜ ፡ ኤልሻዳይ ከሳሾቼ ፡ ቀርበው ፡ ሲቀበጣጥሩ በሆነ ፡ ባልሆነው ፡ ነገር ፡ ሲሽርሩ ጉልበት ፡ የሚያደክም ፡ ልብንም ፡ የሚያርድ ነበረ ፡ ቃላቸው ፡ ቅጥርን ፡ የሚንድ ለልጅህ ፡ እራርተህ ፡ ቁጣህ ፡ በተናቸው ፍፁም ፡ አልተውከኝም ፡ እንደምኞታቸው እነሱ ፡ ወደቁ ፡ ተሰነካከሉ በአንተ ፡ ተደግፌ ፡ አመለጥኩ ፡ ከሁሉ ቀና ፡ አልኩኝ ፡ ከአንገቴ ፡ የልቤ ፡ ደረሰ በየዋሁ ፡ ጌታ ፡ እምባዬ ፡ ታበሰ ያለቀስኩባቸው ፡ እነኛ ፡ ዘመናት አልፌያቸዋለሁ ፡ በጌታዬ ፡ ብርታት ቀና ፡ አደረገኝ ፡ ቀና ፡ የልቤ ፡ ደረሰ በየዋሁ ፡ ጌታ ፡ እምባዬ ፡ ታበሰ ያለቀስኩባቸው ፡ እነኛ ፡ ዘመናት አልፌያቸዋለሁ ፡ በጌታዬ ፡ ብርታት አዝ፦ መልካም ፡ ነህ ፡ ከተባልከው ፡ በላይ (፪x) ስትሰራ ፡ የሌለብህ ፡ ከልካይ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሁልጊዜ ፡ ኤልሻዳይ መልካም ፡ ነህ ፡ ከተባልከው ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ በላይ መልካም ፡ ነህ ፡ ከተባልከው ፡ በላይ ስትሰራ ፡ የሌለብህ ፡ ከልካይ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሁልጊዜ ፡ ኤልሻዳይ አትገመትም ፡ እንደዚህ ፡ ተብለህ በሰው ፡ አይምሮ ፡ መቼ ፡ ተመዝነህ መልካምነትህ ፡ ፍቅርህም ፡ ቢወራ ተነግሮ ፡ አያልቅም ፡ ሁሉም ፡ በየተራ እልፍ ፡ ልሳኖች ፡ ሺህ ፡ ቃል ፡ ቢደረደር ሊገልጥ ፡ አይችልም ፡ ጌታ ፡ የአንተን ፡ ፍቅር አዝ፦ መልካም ፡ ነህ ፡ ከተባልከው ፡ በላይ (፪x) ስትሰራ ፡ የሌለብህ ፡ ከልካይ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሁልጊዜ ፡ ኤልሻዳይ መልካም ፡ ነህ ፡ ከተባልከው ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ በላይ መልካም ፡ ነህ ፡ ከተባልከው ፡ በላይ ስትሰራ ፡ የሌለብህ ፡ ከልካይ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሁልጊዜ ፡ ኤልሻዳይ ቀና ፡ አልኩኝ ፡ ከአንገቴ ፡ የልቤ ፡ ደረሰ በየዋሁ ፡ ጌታ ፡ እምባዬ ፡ ታበሰ ያለቀስኩባቸው ፡ እነኛ ፡ ዘመናት አልፌያቸዋለሁ ፡ በጌታዬ ፡ ብርታት ቀና ፡ አደረገኝ ፡ ቀና ፡ የልቤ ፡ ደረሰ በየዋሁ ፡ ጌታ ፡ እምባዬ ፡ ታበሰ ያለቀስኩባቸው ፡ እነኛ ፡ ዘመናት አልፌያቸዋለሁ ፡ በጌታዬ ፡ ብርታት
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.