Loading
አዝ፦ ከአንተ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ የለምና ፡ ለእኔ አንስቼ ፡ አልጠግብህም ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ ከአንተ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ የለምና ፡ ለእኔ አውርቼ ፡ አልጠግብህም ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ ዘመን ፡ ሲከፋ ፡ ቀን ፡ ሲለዋወጥ አንተ ፡ ግን ፡ ያው ፡ ነህ ፡ የማትለወጥ ሁሉን ፡ ለይቼ ፡ አይቼዋለሁ እንዳንተ ፡ ሚሆን ፡ የት ፡ አገኛለሁ ሲከፋኝ ፡ የማዋይህ ፡ ገበናዬን ፡ የማሳይህ ለክፉ ፡ ቀን ፡ ትሆናለህ ፡ ቢመኩብህ ፡ ታስመካለህ (፪x) አዝ፦ ከአንተ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ የለምና ፡ ለእኔ አንስቼ ፡ አልጠግብህም ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ ከአንተ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ የለምና ፡ ለእኔ አውርቼ ፡ አልጠግብህም ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ ሁሉም ፡ እርቆ ፡ ጀርባ ፡ ሲሰጠኝ ተስፋዬ ፡ ያልኩት ፡ ድንገት ፡ ሲከዳኝ ቀና ፡ አደረከኝ ፡ እጆቼን ፡ ይዘህ ዳግም ፡ አቆምከኝ ፡ እንዲህ ፡ ሸላልመህ ሲከፋኝ ፡ የማዋይህ ፡ ገበናዬን ፡ የማሳይህ ለክፉ ፡ ቀን ፡ ትሆናለህ ፡ ቢመኩብህ ፡ ታስመካለህ (፪x) አዝ፦ ከአንተ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ የለምና ፡ ለእኔ አንስቼ ፡ አልጠግብህም ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ ከአንተ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ የለምና ፡ ለእኔ አውርቼ ፡ አልጠግብህም ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ ቀን ፡ የጣለውን ፡ እዩት ፡ ይሄን ፡ ሰው ብለው ፡ ሲያወሩ ፡ መነሻም ፡ የለው ለክፉ ፡ ቀን ፡ ነህ ፡ መኩሪያ ፡ መከታ እያዩኝ ፡ ወጣሁ ፡ ወደ ፡ ከፍታ ሲከፋኝ ፡ የማዋይህ ፡ ገበናዬን ፡ የማሳይህ ለክፉ ፡ ቀን ፡ ትሆናለህ ፡ ቢመኩብህ ፡ ታስመካለህ (፪x) አዝ፦ ከአንተ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ የለምና ፡ ለእኔ አንስቼ ፡ አልጠግብህም ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ ከአንተ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ የለምና ፡ ለእኔ አውርቼ ፡ አልጠግብህም ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.