Loading
ስፍራን ፡ አዘጋጅተህ ፡ እኔን ፡ ከጠራኀኝ በክብር ፡ እንድኖር ፡ ወደኅኝ ፡ ከአዳንከኝ ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ ቀርበኀኛልና ውዴ ፡ ተቀበለኝ ፡ የልቤን ፡ ምሥጋና አዝ:- በዋጋ ፡ ገዝተኀኛል ፡ ከእንግዲህ ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል የዚች ፡ ምድር ፡ አይደለሁምና በስምህ ፡ ላብዛልህ ፡ ምሥጋና በደሌን ፡ ሽረሃል ፡ እኔን ፡ ግን ፡ ወደሃል ሞቴን ፡ ወስደህ ፡ ከእኔ ፡ ሞትክልኝ ፡ መድህኔ (፪x) የዳነን ፡ ማንነት ፡ ከአንተ ፡ አግኝቻለሁ ሥጋቴን ፡ ጭንቀቴን ፡ ለአንተው ፡ ትቼዋለሁ ፍፁም ፡ ሰላም ፡ በአንተ ፡ ከአንተ ፡ ሆኖልኛል ለዘለዓለም ፡ መኖር ፡ መብቱ ፡ ተሰጥቶኛል አዝ:- በዋጋ ፡ ገዝተኀኛል ፡ ከእንግዲህ ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል የዚች ፡ ምድር ፡ አይደለሁምና በስምህ ፡ ላብዛልህ ፡ ምሥጋና በደሌን ፡ ሽረሃል ፡ እኔን ፡ ግን ፡ ወደሃል ሞቴን ፡ ወስደህ ፡ ከእኔ ፡ ሞትክልኝ ፡ መድህኔ (፪x) የፈሰሰልኝ ፡ ደም ፡ በእውነት ፡ ደምህ ፡ ነው ሕይወት ፡ የሆነልኝ ፡ ሙት ፡ ለነበርኩት ፡ ሰው እንዳልጠፋ ፡ አድርገህ ፡ አንተ ፡ አድነኀኛል ላደረክልኝ ፡ ሁሉ ፡ መልሴ ፡ ያንስብሃል አዝ:- በዋጋ ፡ ገዝተኀኛል ፡ ከእንግዲህ ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል የዚች ፡ ምድር ፡ አይደለሁምና በስምህ ፡ ላብዛልህ ፡ ምሥጋና በደሌን ፡ ሽረሃል ፡ እኔን ፡ ግን ፡ ወደሃል ሞቴን ፡ ወስደህ ፡ ከእኔ ፡ ሞትክልኝ ፡ መድህኔ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.