Loading
ሊያገለግልህ ፡ የጠራኸው ፡ በህዝብህ ፡ ፊት ፡ የሾምከው ስንቱ ፡ ርቆህ ፡ ያገለግላል ፡ ለዝናው ፡ ክብሩ ፡ አድሮ ፡ ይዉላል ስንቱ ፡ ርቆህ ፡ የራሱን ፡ ክብር ፡ ያገለግላል ለዝናው ፡ ስሙ ፡ ታግሎ ፡ ይኖራል ፡ ያላንተ ፡ ጉዞ ፡ ስም ፡ ዝናን ፡ ብቻ ፡ ይዞ የስጋ ፡ ጥረት ፡ በሌለህበት ያላንተ ፡ ክብር ፡ በእኔነት ፡ ፍቅር በፀጋ ፡ ካባ ፡ ለራስ ፡ ወከባ ለከንቱ ፡ መንገድ ፡ ባንተ ፡ ሲነገድ ፍለጋ ፡ ክብርን ፍለጋ ፡ ዝናን ፍለጋ ፡ ብልጫን ፡ ፍለጋ ፍለጋ ፡ ንዋይን ፍለጋ ፡ ትኩረትን ፍለጋ ፡ ፍለጋ አምልኮተ ፡ ዝና ፡ አምልኮተ ፡ እኔ በአምልኮ ፡ መልክ ፡ ሽፋን ፡ በፍቅሬ ፡ ተይዤ በንጉስ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ህዝብ ፡ ላይ በውድድር ፡ መንፈስ ፡ ምስባክ ፡ ለታይታ ፡ በትወና ፡ ህይወት ፡ የኔን ፡ ለኔ ፡ ዋይታ ፍለጋ ፡ ክብርን ፍለጋ ፡ ዝናን ፍለጋ ፡ ብልጫን ፡ ፍለጋ ፍለጋ ፡ ንዋይን ፍለጋ ፡ ትኩረትን ፡ ፍለጋ ፡ ፍለጋ በሌለህበት ፡ ሳውልህ ፡ ለዝና ፡ ስሜ ፡ ስፈልግህ ተላላ ፡ የልቤን ፡ ባያገኘው ፡ ካንተ ፡ ማን ፡ ሊሰውረው ከባዶ ፡ ጩኸት ፡ ከሌለህበት ፡ ዝምታዬ ፡ ካገነነህ ፡ ባለህበት ፡ ክብሬ ፡ ያ ፡ ነው ፡ ያከበረህ ፡ እኔነቴን ፡ የሰበረ ፍለጋዬ ፡ ይሁን ፡ ለጉዳይህ ፍለጋዬ ፡ ይሁን ፡ ለሀሳብህ ፍለጋዬ ፡ ፍለጋዬ ፡ ፡ ይሁን ፡ ለክብርህ ስራዬን ፡ ትመዝናለህ ፡ ከመንበርህ ፡ ታዬኛለህ ፍለጋዬን ፡ አጥራው ፡ መንገዴን ፡ ላረካ ፡ የቆምኩለትን ፡ የራስ ፡ ጥሜን መከሩ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ስራ ፡ አለ ፡ በቤቱ ወደሞት ፡ ሚነዳ ፡ አለ ፡ በየዕለቱ በራስ ፡ ፍቅር ፡ ታምሜ ፡ መሽቶብኝ ፡ ይነጋል ኢየሱስን ፡ ሳያይ ፡ ስንቱን ፡ ሞት ፡ ይቀድማል እድሜያችን ፡ ቢበዛ ፡ ሰባ ፡ ነው ፡ ቢያልፍ ፡ እንኳን ፡ ሰማኒያ ምን ፡ አለን ፡ ክብር ፡ ምን ፡ አለን ፡ ንዋይ ኢየሱስ ፡ ካንተ ፡ ወዲያ ምን ፡ አለን ፡ ዝና ፡ ምን ፡ አለን ፡ ክብር ፡ ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ ወዲያ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.