Loading
አዝ፦ በማለዳ ፡ ምሥጋናዬ ፡ በሌሊትም ፡ ዝማሬዬn ይዤ ፡ ልቅረብ ፡ ወደ ፡ ፊትህ ቤትህን ፡ ይሙላው ፡ ያውድልህ (፪x) ሰዎች ፡ ሰውን ፡ አይተው ፡ ያፈገፍጋሉ የሕይወትን ፡ መንገድ ፡ ጥለው ፡ ይሄዳሉ እኔ ፡ ግን ፡ ባሰብኝ ፡ ጨመረብኝ ፡ ፍቅሩ አልሻም ፡ ለሰከንድ ፡ መውጣት ፡ ከድንበሩ አልሻም ፡ ለሰከንድ ፡ መውጣት ፡ ከድንበሩ እልሻም ፡ ለሰከንድ ፡ መውጣት ፡ ከክልሉ (፪x) አዝ፦ በማለዳ ፡ ምሥጋናዬ ፡ በሌሊትም ፡ ዝማሬዬ ይዤ ፡ ልቅረብ ፡ ወደ ፡ ፊትህ ቤትህን ፡ ይሙላው ፡ ያውድልህ (፪x) በምድር ፡ እስካለሁ ፡ እኔ ፡ እናገራለሁ ብዙ ፡ ተደርጐልኝ ፡ ብዙ ፡ አይቻለሁ የማይገባኝን ፡ ሆኖልኝ ፡ እያየሁ ክብር ፡ ለሚገባው ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ እላለሁ ጐንበስ ፡ ቀና ፡ ብዬ ፡ አመልከዋለሁ (፬x) እኔስ (፬x) ፡ እኔስ ፡ እንደገና ፡ ቃልን ፡ እገባለሁ ሃሳብህን ፡ ይዤ ፡ ሃሳቤን ፡ እጥላለሁ የወደድከው ፡ ይሁን ፡ አባ ፡ እኔ ፡ እኔ ፡ እታዘዛለሁ አንተን ፡ ደስ ፡ ካለህ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እፈልጋለሁ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.