Loading
ወረቀት ፡ ብዕሬን ፡ አገናኘሁኝ ስለጌታ ፡ ውለታ ፡ መጻፍ ፡ አሰኘኝ የትኛውን ፡ ጽፌ ፡ የቱን ፡ ልተወው የምለውን ፡ ባጣ ፡ እንዲህ ፡ ልበለው ፡ ልበለው ባለውለታዬ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፬x) ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የማልመልሰው የእግዚአብሄር ፡ ልጅ ፡ ለእኔ ፡ የሰራው ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰፊ ፡ ጊዜ ፡ ያሻኛል እንኳን ፡ ቀኑ ፡ ዘላለም ፡ ያንሰኛል ታሪክ ፡ የሌለውን ፡ ባለታሪክ ጠላት ፡ የሆንኩት ፡ ወዳጅ ፡ አረክ አሳዳጅ ፡ የሆንኩትን ፡ ነካኽኝና በቅዱሳኑ ፡ ፊት ፡ አቆምከኝና ዘምር ፡ አልከኝ (፬x) በስንኝ ፡ ቋጠሮ ፡ ችዪ ፡ ላልሰንቅ ጠልቄ ፡ ባስብም ፡ አቅሜ ፡ እስኪያልቅ አወይ ፡ በትንሿ ፡ በዚች ፡ ወረቀት ጭሬ ፡ አልጨርሰው ፡ የሱን ፡ ሰጪነት ፡ ለጋስነት መካኒቱ ፡ ሰባት ፡ ወለደች ሳራም ፡ በእርጅና ፡ ጸነሰች ሙሴን ፡ በጥበብ ፡ አሳደገ ምስኪኑን ፡ ዳዊት ፡ ንጉሥ ፡ አደረገ እንደዚህ ፡ ነው ፡ የኢየሱስ ፡ ስራ አይጨረስ ፡ ሁሌም ፡ ቢወራ እኔም ፡ አለኝ ፡ የምለው አግኝቶኛል ፡ ውለታው ባለውለታዬ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፬x) ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የማልመልሰው የእግዛብሄር ፡ ልጅ ፡ ለእኔ ፡ የሰራው ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰፊ ፡ ጊዜ ፡ ያሻኛል እንኳን ፡ ቀኑ ፡ ዘላለም ፡ ያንሰኛል ብዙ ፡ ነው ፡ የሱ ፡ ውለታ ሳስበው ፡ ጥዋት ፡ እና ፡ ማታ ግርም ፡ ይለኛል ፡ ድንቅ ፡ ይለኛል ፡ ቃላት ፡ ያጥረኛል በምን ፡ ቋንቋ ፡ ነው ፡ በምን ፡ አንደበት የምገልጸው ፡ የሱን ፡ በጐነት (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.