Loading
አዝ:- የኢየሱስ ደም {ዛሬም ትኩስ ነው} 2x
አማላጄ ነው
የጌታዬ ደም {ዛሬም ትኩስ ነው} 2x
አማላጄ ነው
የሰው ዘር ሁሉ የአዳም ስህተት
ይዞት ወደቀ {ወደ ጥፋት} 2x
ማንም እንዳይድን ይሄን ቢረዳ
ሊከፍለው መጣ {ለሃጥያት እዳ} 2x
የሃጥያት ደሞዝ ነውና ሞት
ሞቴን ሞተልኝ {ሰጠኝ ህይወት} 2x
ሃጥያት ተሻረ ከኔ ላይ
በፈሰሰልኝ ጎልጎታ ላይ {ቀራንዮ ላይ} 2x
በገዛ ደሙ እርቅ አወረደ
የጠፋሁትን ስለወደደ
ሃጥዕ ተብዬ ስም ለወጣልኝ
በደሙ አንፅቶ ጻድቅ አስባለኝ
ከደጉ አባቴ አሁን ታረቅኩ
በቅዱስ ደሙ ስለታጠብኩ
ሌላ አማላጅ ሳያስፈልገኝ
በቀኙ ሆንኩኝ ደሙ አቀረበኝ
የኢየሱስ ደም ሳያስታርቀኝ
የማን ጸሎት ነው የሚያስታርቀኝ
የኢየሱስ ደም ያላጠበኝ
የማን ጸሎት ነው የሚያጥበኝ
የኢየሱስ ደም ሳያስታርቀኝ
የማን ምልጃ ነው የሚያስታርቀኝ
የኢየሱስ ደም ያላነፃኝ
የማን ጸሎት ነው የሚያነፃኝ
አዝ:- {ያስታረቀኝ ከአባቱ አማላጅ የሆነልኝ
ስለሃጥያቴ ጥብቅና በአብ ፊት የቆመልኝ} 2x
ለሆንኩት ለኔ ለሞት ፍርደኛ
በአብ ቀኝ ያለ አንዱ ብቸኛ
ስለበደሌ እሱ ነው ዋሴ
የሚቆምልኝ ልክ እንደ ራሴ
መሰላል ያየው ያዕቆብ በህልሙ
መካከለኛ ነው ክቡር ደሙ
ሰማይ ከኔ ጋር እርቅ ያደረገው
በማንም አይደል በኢየሱስ ደም ነው
{ስደክም የሚያበረታኝ
በውድቀቴ የማይስቅብኝ
በፍቅር ዓይኖቹ የሚያየኝ
ደጉ ሊቀ ካህን አለኝ} 2x
አዝ:- {{ሊቀ ካህኔ ኢየሱሴ} 2x
ጠበቃዬ ኢየሱሴ
አለልኝ በሰማይ ለነፍሴ} 2x
{የልጅነት አባት የሆነኝ
እንዳልወድቅ የቆመልኝ
ካህኔ ጠባቂ የነፍሴ
ይወደኛል የሞተልኝ/ኣማላጄ ኢየሱሴ} 2x
{ታማኙ የነፍሴ ጠባቂ
ኢየሱስ ለእኔ አዋቂ
ዳኛዬ ቅኑ ፈራጄ
ኢየሱስ እርሱስ ወዳጄ} 2x
የልጅነት አባት የሆነኝ
እንዳልወድቅ የቆመልኝ
ካህኔ የነፍሴ ጠባቂ
ኢየሱስ ለእኔ አዋቂ
{ጉድ አሉ የሚያውቁኝ በሙሉ
በመቆሜ ሁሉም ተገረሙ
እኔ ግን እንደዚህ እላለሁ
መቆሜ ከእርሱ የተነሳ ነው} 2xComments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.