Loading
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ኖሬ ፡ አንተን ፡ አስከብሬ ፡ ፍሬን ፡ እንዳፈራ ነበረ ፡ ምኞትህ ፡ ያሁሉ ፡ ልፋትህ ፡ እኔን ፡ ስትሰራ ቅጠሉ ፡ እንዳማረ ፡ ግን ፡ ፍሬ ፡ እንደሌለው ፡ በለስ ፡ ሆኛለሁ ጥቂት ፡ ታገሰኝ ፡ አንድ ፡ እድል ፡ ስጠኝ ፡ ፊትህ ፡ ወድቄያለሁ እንዳትተወኝ ፡ እማጸናለሁ ከተውከኝማ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ (፪x) ባጠፋ ፡ እንኳ ፡ ቆንጥጠህ ፡ መልሰኝ ብበድልህ ፡ እንኳ ፡ ገስጸህ ፡ መልሰኝ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ያለአንተ ፡ ማን ፡ አለኝ ድንጋዩን ፡ ልቤን ፡ ባክህ ፡ አውጣልኝ ፡ አባ ፡ እባክህ ፡ አውጣልኝ አዲስን ፡ መንፈስ ፡ በውስጤ ፡ አኑርልኝ ፡ ጌታ ፡ በውስጤ ፡ አኑርልኝ ድምጽህን ፡ ስሰማ ፡ አው ፡ አልሁን ፡ እልኸኛ ቸል ፡ ብዬ ፡ እንዳልጠፋ ፡ አባ ፡ እባክህ ፡ አንቃኛ እባክህ ፡ አንቃኛ (፪x) የሰጠኸኝን ፡ ያንን ፡ አደራ ፡ ያንን ፡ መክሊት ነበር ፡ ነቅቼ ፡ እንድጠብቅህ ፡ ብዙ ፡ አትርፌበት ምንም ፡ ሳልሰራ ፡ እንደቀበርኩት ፡ ምጻትህ ፡ ቀርቧል አንቃኝ ፡ ጌታዬ ፡ ከስንፍናዬ ፡ ኋላ ፡ እንዳልጣል ዝም ፡ እንዳትለኝ ፡ እማጸናለሁ ዝም ፡ ካልክማ ፡ እኔ ፡ እፈራለሁ (፪x) አባ ፡ አድነኝ ፡ ከቁጣህ ፡ አድነኝ አድነኝ ፡ ኢየሱስ ፡ አድነኝ ለጠፊው ፡ ዓለም ፡ ስጥር ፡ ስለፋ ፡ ጊዜዬ ፡ አልቆ ሠማያዊውን ፡ የዘለዓለሙን ፡ ልቤ ፡ ዘንግቶ ኃይሌ ፡ ተሟጦ ፡ ዘይቴ ፡ አልቆ ፡ ባዶ ፡ ሆኛለሁ ማረኝ ፡ አባቴ ፡ ገባኝ ፡ ጥፋቴ ፡ እመለሳለሁ እኔን ፡ ለምኞቴ ፡ አትስጠኝ ፡ ጌታዬ ፡ አትስጠኝ ፡ ጌታዬ እኔን ፡ ለሥጋዬ ፡ አትስጠኝ ፡ አባዬ ፡ አጽጠኝ ፡ አባዬ እግዚአብሔርን ፡ መፍራት ፡ ጠፍቶ ፡ የለም ፡ ወይ ምኞቱን ፡ የሚያረግ ፡ ሞልቶ ፡ የለም ፡ ወይ ባክህ ፡ በዚህ ፡ ዘመን ፡ አባ ፡ አስተዋይ ፡ አድርገኝ ወደ ፡ ጽድቅ ፡ ጐዳና ፡ አሃ ፡ እግሬን ፡ መልስልኝ አድነኝ ፡ አባ ፡ አድነኝ ፡ ኢየሱስ አድነኝ ፡ ጌታ ፡ አድነኝ ፡ አን..
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.