Loading
በአምሳልህ ፡ የተሠራ ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ ክቡር ፡ ነው መራብ ፡ መሰደዱ ፡ መሞቱ ፡ ለምን ፡ ነው? ምድራችንን ፡ ማራት ፡ እባክህ ፡ አምላካችን ንስሃ ፡ እንገባለን ፡ በፊትህ ፡ ሁላችን አዝ፦ ሰላም (፬x) ፡ ለምድራችን ስለ ፡ አባቶች ፡ በደል ፡ ማረን ፡ እንላለን ስለ ፡ ልጆች ፡ በደል ፡ ማረን ፡ እንላለን ጦርነት ፡ ከምድር ፡ ጩኸት ፡ ዋይታው ፡ ይብቃ ጨለማችን ፡ በርቶ ፡ በሰላም ፡ ይተካ አዝ፦ ሰላም (፬x) ፡ ለምድራችን (፪x) የሰላሙን ፡ አየር ፡ ሁሉም ፡ ተጠምቶታል ጦርነት ፡ ስደትን ፡ ጆሮው ፡ ሰልችቶታል የሰላም ፡ አለቃ ፡ ሁሉም ፡ በእጅህ ፡ ነው ምድራችንን ፡ ማራት ፡ ሰላሟ ፡ በአንተ ፡ ነው አዝ፦ ሰላም (፬x) ፡ ለምድራችን ትምክህት ፡ እልሃችን ፡ ይራቅ ፡ ከእኛ ፡ ይጥፋ ፍቅር ፡ መተሳሰብ ፡ በምድራችን ፡ ይስፋ ጦርነትን ፡ ሻረው ፡ ቀስቱንም ፡ ስበረው ሰላም ፡ ለሰው ፡ ልጆች ፡ ባይበሉም ፡ ጥጋብ ፡ ነው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.