Loading
ምሕረቱ ፡ ገንኖ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ መልካም ፡ የሆነውን ፡ ቀን ፡ እንዳይ ጨለማዬን ፡ ሁሉ ፡ አብርቶአል ፡ ሃዘን ፡ ትካዜም ፡ ከእኔ ፡ ርቋል አንደበቴን ፡ ልክፈት ፡ ልናገር ፡ ያደረገልኝን ፡ ድንቅ ፡ ነገር መልካምነቱ ፡ ህሉ ፡ ይሰማ ፡ በእርሱ ፡ ዘንድ ፡ ዓይኖርም ፡ ጨለማ እርሱ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ እርሱ ፡ የእኔ ፡ እረኛ (፪) ለምን ፡ እሰጋለሁ ፡ ለምን ፡ ልቤ ፡ ይፍራ ዓለቴ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ጽኑ ፡ ነው ፡ መሠረቴ እኔ ፡ ክፉን ፡ አልፈራም ፡ ኢየሱስ ፡ አለ ፡ በሕይወቴ ሃላፊው ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ልረፍ ፡ እንጂ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ አሰጋኝ? ብጨነቅ ፡ ባወጣው ፡ ባወርደው ፡ አንድም ፡ የለም ፡ የምጨምረው ታማኝ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ እረኛ ፡ የማይደክም ፡ ከቶ ፡ የማይተኛ ሃሣቤን ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ እጥላለሁ ፡ ይረዳኛል ፡ አምኜዋለሁ በቸርነቱ ፡ እጄን ፡ ይዞ ፡ ትላንትናን ፡ እንዳሳለፈኝ ለዛሬውም ፡ አምላኬ ፡ አለልኝ ፡ ለምን ፡ ልፍራ ፡ ምን ፡ አስጨነቀኝ? ምሕረቱና ፡ ቸርነቱ ፡ ሁልጊዜ ፡ ይከተሉኛል አይተወኝም ፡ ለዘለዓለም ፡ ኢየሱሴ ፡ ቃል ፡ ገብቶልኛል
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.