Loading
አዝ፦ ኧረ ፡ ተው ፡ ወንድሜ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበል ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተል ኧረ ፡ ተይ ፡ እህቴ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበይ ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተይ አያዋጣም ፡ እዚም ፡ እዚያም መረጋገጥ ፡ እንዲያው ፡ መዋተት ትርፉ ፡ ሞት ፡ ነው ፡ ተው ፡ ወንድሜ አያዛልቅ ፡ በኃጢአት ፡ መዋኘት ወስነህ ፡ ተቀበል ፡ ጌታን ፡ በልብህ ኃጢአት ፡ አያባብለህ ፡ ጨክነህ ፡ ተወው ፡ ተወው ፡ ይቅርብህ አዝ፦ ኧረ ፡ ተው ፡ ወንድሜ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበል ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተል ኧረ ፡ ተይ ፡ እህቴ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበይ ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተይ የዓለም ፡ ኑሮ ፡ እሽኮለሌው እያሳሳቀ ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ነው ይልቅ ፡ ንቃ ፡ ዛሬ ፡ ወስን ሞት ፡ እንደው ፡ ቀጠሮ ፡ የለው ለሕይወትህ ፡ ሰላም ፡ አግኝ ፡ እረፍትን ና ፡ ብሎ ፡ ሲጠራ ፡ ዛሬ ፡ ነገ ፡ አትበል ፡ ስጠው ፡ ልብህን አዝ፦ ኧረ ፡ ተው ፡ ወንድሜ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበል ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተል ኧረ ፡ ተይ ፡ እህቴ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበይ ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተይ ሀብት ፡ ቢሞላ ፡ ቢትረፈረፍ ለነፍስ ፡ አንድም ፡ ጠብታ ፡ የለው አንተነትህን ፡ የሚያረካ ካለ ፡ ኢየሱስ ፡ ሁሉም ፡ ዘበት ፡ ነው እረኝነቱ ፡ ሥር ፡ መጥተህ ፡ ተጠለል ኢየሱስን ፡ ምረጠው ፡ ለነፍስ ፡ ለሥጋህ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ አትበል አዝ፦ ኧረ ፡ ተው ፡ ወንድሜ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበል ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተል ኧረ ፡ ተይ ፡ እህቴ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበይ ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተይ ና ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ጌታ ፡ ይፈታል አንተነትህን ፡ ይለውጣል በአዲስ ፡ ሕይወት ፡ በአዲስ ፡ ኑሮ ልብህን ፡ ደስታ ፡ ይሞላል ሰላምህ ፡ እንደ ፡ ወንዝ ፡ ሞልቶ ፡ ይፈሳል ዋጋ ፡ አትከፍልበትም ፡ ወስን ፡ ወንድሜ ፡ ጌታ ፡ ይሻላል አዝ፦ ኧረ ፡ ተው ፡ ወንድሜ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበል ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተል ኧረ ፡ ተይ ፡ እህቴ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበይ ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተይ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.