Loading
አዝ:- ፍጥረት ፡ የሚደገፍበት እኔም ፡ ተስፋ ፡ ማደርግበት ጌታ ፡ ነው ፡ እንከን ፡ የሌለበት ልዘምር ፡ እስቲ ፡ ልቀኝለት ለሕይወት ፡ ጥያቂ ፡ ለእንቆቅልሹ ጌታ ፡ ነው ፡ ምላሽ ፡ አቻ ፡ የለሹ ሁሉንም ፡ መልካም ፡ ያደርገውና ያስገርመናል ፡ ድንቅ ፡ ይሰራና ያድንና (ኦሆሆሆሆ) ፤ ይባርክና (ኦሆሆሆሆ) ሰው ፡ ያደርግና (ኦሆሆሆሆ) ፤ ያቆምና (ኦሆሆሆሆ) ይደግፍና እየባረኩኝ ፡ እባርክሃለሁ በሕይወትህ ፡ ድንቅን ፡ አደርጋለሁ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ አትፍራ ፡ እንዳልከኝ የኔ ፡ ጌታ ፡ ስንቱን ፡ አሳለፍከኝ ስንት ፡ ጊዜ ፡ አዳንከኝ ፡ ከጥፋት ልገልጽ ፡ አልችል ፡ የውለታህን ፡ ብዛት ድንቅን ፡ አይቻለሁ ፡ ድንቅን ፡ አይቻለሁ በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ ገና ፡ አመልክሃለሁ ድንቅን ፡ አይቻለሁ ፡ ድንቅን ፡ አይቻለሁ በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ እገዛልሃለሁ አዝ:- ፍጥረት ፡ የሚደገፍበት እኔም ፡ ተስፋ ፡ ማደርግበት ጌታ ፡ ነው ፡ እንከን ፡ የሌለበት ልዘምር ፡ እስቲ ፡ ልቀኝለት ለሕይወት ፡ ጥያቂ ፡ ለእንቆቅልሹ ጌታ ፡ ነው ፡ ምላሽ ፡ አቻ ፡ የለሹ ሁሉንም ፡ መልካም ፡ ያደርገውና ያስገርመናል ፡ ድንቅ ፡ ይሰራና ያድንና (ኦሆሆሆሆ) ፤ ይባርክና (ኦሆሆሆሆ) ሰው ፡ ያደርግና (ኦሆሆሆሆ) ፤ ያቆምና (ኦሆሆሆሆ) ይደግፍና ቁሻሻውን ፡ ታሪኬን ፡ ለውጠህ ሰው ፡ አደረከኝ ፡ ኢየሱስ ፡ በእኔ ፡ ከብረህ ገና ፡ ህጻን ፡ ሳለሁ ፡ የተሸከምከኝ በጉያህ ፡ ውስጥ ፡ እስካሁን ፡ አለሁኝ አልተውህም ፡ አልጥልህም ፡ ያልከኝ ኢየሱሴ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ ድንቅን ፡ አይቻለሁ ፡ ድንቅን ፡ አይቻለሁ በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ ገና ፡ አመልክሃለሁ ድንቅን ፡ አይቻለሁ ፡ ድንቅን ፡ አይቻለሁ በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ እገዛልሃለሁ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.