Loading
አዝ፦ ዘምር ፡ አለኝ (፬x) ሥራህ ፡ ተሰርቷል ፡ ዘምር ቀንበር ፡ ተሰብሯል ፡ ዘምር ማልቀስ ፡ አበቃ ፡ ዘምር እኔ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ ዘምር (፪x) አለኝ የሚያስለቅስህን ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ጣለው ፡ ብሎኛል (፪x) እርሱ ፡ እያለ ፡ ለምን ፡ ልሥጋ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ከእኔ ፡ ጋራ የማምለጫ ፡ ዓለቴ ፡ ነው ጋሻዬና ፡ ምርኩዜም ፡ ነው (፪x) አዝ፦ ዘምር ፡ አለኝ (፬x) ሥራህ ፡ ተሰርቷል ፡ ዘምር ቀንበር ፡ ተሰብሯል ፡ ዘምር ማልቀስ ፡ አበቃ ፡ ዘምር እኔ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ ዘምር (፪x) አለኝ እኔ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ አትስጋ ፡ ብሎኛል ፡ እርሱ (፪x) አልደነግጥ ፡ ከቶ ፡ አልፈራ ባለ ፡ ድል ፡ ነኝ ፡ ከአምላክ ፡ ጋራ ጠላቶቼ ፡ ሰምጠው ፡ ቀሩ አሻገረኝ ፡ ኢኸው ፡ ለክብሩ (፪x) አዝ፦ ዘምር ፡ አለኝ (፬x) ሥራህ ፡ ተሰርቷል ፡ ዘምር ቀንበር ፡ ተሰብሯል ፡ ዘምር ማልቀስ ፡ አበቃ ፡ ዘምር እኔ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ ዘምር (፪x) አለኝ ሁሌ ፡ ደስ ፡ ይበልህ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ ይበልህ ፡ አለኝ፪ መቆዘሜ ፡ ለምንድን ፡ ነው መተከዜስ ፡ ለምንድን ፡ ነው ለሚያልፈው ፡ ለዚህ ፡ ምድር መዘመር ፡ ነው ፡ ለእርሱ ፡ ክብር (፪x) አዝ፦ ዘምር ፡ አለኝ (፬x) ሥራህ ፡ ተሰርቷል ፡ ዘምር ቀንበር ፡ ተሰብሯል ፡ ዘምር ማልቀስ ፡ አበቃ ፡ ዘምር እኔ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ ዘምር (፪x) አለኝ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.