Loading
አዝ፦ የመስቀሉ ፡ ፍቅር (፬x) የመስቀሉ ፡ ፍቅር (፬x) ለእኔ ፡ ነው ፡ መንክራተቱ መስቀል ፡ ላይ ፡ ውሎ ፡ መሞቱ ያኔ ፡ የፈሰሰው ፡ ደሙ አኑሮኛል ፡ ዛሬም ፡ በቤቱ እንደሚታረድ ፡ በግ ፡ ዝም ፡ ያለው ግርፋት ፡ ስቃዩ ፡ ለእኔ ፡ ነው ሞቴን ፡ የሞተልኝ ፡ በጐልጐታ ውርደቴን ፡ ተዋርዶ ፡ ክፉን ፡ መታ በሕይወት ፡ አለሁኝ ፡ ዛሬም ፡ በዚህ ፡ ጌታ አዝ፦ የመስቀሉ ፡ ፍቅር (፬x) የመስቀሉ ፡ ፍቅር (፬x) ለእኔ ፡ ነው ፡ መንክራተቱ መስቀል ፡ ላይ ፡ ውሎ ፡ መሞቱ ያኔ ፡ የፈሰሰው ፡ ደሙ አኑሮኛል ፡ ዛሬም ፡ በቤቱ ክቡር ፡ ሆኖ ፡ ሳለ ፡ የከበረ ጌታዬ ፡ ስለእኔ ፡ ራሱን ፡ ጣለ እርቃኑን ፡ ሰቀሉት ፡ በእንጨት ፡ ላይ ሃፍረቴን ፡ ሸፈነው ፡ እርሱ ፡ ሊታይ ዝቅ ፡ አለ ፡ ወረደ ፡ ያ ፡ ኤልሻዳይ አዝ፦ የመስቀሉ ፡ ፍቅር (፬x) የመስቀሉ ፡ ፍቅር (፬x) ለእኔ ፡ ነው ፡ መንክራተቱ መስቀል ፡ ላይ ፡ ውሎ ፡ መሞቱ ያኔ ፡ የፈሰሰው ፡ ደሙ አኑሮኛል ፡ ዛሬም ፡ በቤቱ ስለእኔ ፡ ያለው ፡ ፍቅር ፡ ስለልጁ ነፍሱን ፡ እስከመስጠት ፡ ነበር ፡ እርሱ የእኔን ፡ በደል ፡ ጌታ ፡ ተሸከመ ተራራውን ፡ ወጣ ፡ ብዙ ፡ ደከመ ያኔ ፡ ቀራንዮ ፡ ሁሉ ፡ ተፈጸመ አዝ፦ የመስቀሉ ፡ ፍቅር (፬x) የመስቀሉ ፡ ፍቅር (፬x) ለእኔ ፡ ነው ፡ መንክራተቱ መስቀል ፡ ላይ ፡ ቅሎ ፡ መሞቱ ያኔ ፡ የፈሰሰው ፡ ደሙ አኑሮኛል ፡ ዛሬም ፡ በቤቱ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.