Loading
ብቻዬን ፡ ቁጭ ፡ ብዬ ፡ አዝኜ ፡ በቤቴ በጣም ፡ እያመመኝ ፡ ይሄው ፡ ስብራቴ በድንገት ፡ ኢየሱስ ፡ ደረሰልኝ ሰባራውን ፡ ጠጋኝ ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ የደካሞች ፡ አሳራፊ ኢየሱስ ፡ አለ ፡ ነፍሴ ፡ እረፊ ሸክም ፡ ከብዶበት ፡ የሚንገላታ ወደዚህ ፡ ጌታ ፡ መጥቶ ፡ ይበርታ ዓይኔን ፡ አንስቼ ፡ ከሰው ፡ ላይ ሀዘኔን ፡ ረሳሁ ፡ ኢየሱስን ፡ ሳይ አዝ:- ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ከሞት ፡ መዳኛዬ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ የዓይኔ ፡ ማረፊያዬ የፈተና ፡ መዓት ፡ በላዬ ፡ ቢፈስ ፀሎቴም ፡ በሙሉ ፡ ባይመለስ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ እላለሁ ፡ ሌላ ፡ አያምረኝም ቤዛዬን ፡ ኢየሱስ ፡ በፍፁም ፡ አልክድም (፪x) አዝ:- ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ የዓይኔ ፡ ማረፊያዬ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ከሞት ፡ መዳኛዬ ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ከሞት ፡ መዳኛዬ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ የዓይኔ ፡ ማረፊያዬ ኃጢአተኛ ፡ ሳለሁ ፡ ሰዎች ፡ ሲገፉኝ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ አይቶ ፡ ራራልኝ እንደ ፡ ኃጢአቴ ፡ ያልፈረደብኝ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ እርሱ ፡ ለእኔ ፡ አዘነልኝ አዝ:- ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ የዓይኔ ፡ ማረፊያዬ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ከሞት ፡ መዳኛዬ ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ከሞት ፡ መዳኛዬ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ የዓይኔ ፡ ማረፊያዬ የደካሞች ፡ አሳራፊ ኢየሱስ ፡ አለ ፡ ነፍሴ ፡ እረፊ ሸክም ፡ ከብዶበት ፡ የሚንገላታ ወደዚህ ፡ ጌታ ፡ መጥቶ ፡ ይበርታ ዓይኔን ፡ አንስቼ ፡ ከሰው ፡ ላይ ሀዘኔን ፡ ረሳሁ ፡ ኢየሱስን ፡ ሳይ አዝ:- ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ከሞት ፡ መዳኛዬ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ የዓይኔ ፡ ማረፊያዬ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.