Loading
አዝ:- ፀጋው ፡ ነው ፡ እኔን ፡ የሚያቆመኝ ምህረቱ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ የሚያዘምረኝ (፪x) ሁልጊዜ ፡ ችኩል ፡ ነው ፡ ሲያዩት ፡ ደፋር ፡ መሳይ ዶሮ ፡ ሳይጮህ ፡ በፊት ፡ ሶስት ፡ ጊዜ ፡ ክህዶታል በሰው ፡ አይን ፡ ቢሆን ፡ ይህ ፡ ሰው ፡ ከሀዲ ፡ ነው የፀጋው ፡ ጉልበት ፡ ግን ፡ ዳግም ፡ ሰው ፡ አረገው አዝ:- ፀጋው ፡ ነው ፡ እኔን ፡ የሚያቆመኝ ምህረቱ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ የሚያዘምረኝ (፪x) ቢሆንማ ፡ ኑሮ ፡ በክብር ፡ በዝና በገንዘብም ፡ ብዛት ፡ ብዙ ፡ ብልጥግና እንዴት ፡ እሆን ፡ ነበር ፡ እርቆኝ ፡ መዳኔ ግን ፡ እንዲያው ፡ ወደደኝ ፡ አሰበኝ ፡ መድህኔ እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ጌታዬ ፡ ልዩ ፡ ነው የተረሳውን ፡ ሰው ፡ እንዲህ ፡ ሚያስታውሰው አዝ:- ፀጋው ፡ ነው ፡ እኔን ፡ የሚያቆመኝ ምህረቱ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ የሚያዘምረኝ (፪x) በማይመስል ፡ ነገር ፡ መስራት ፡ የሚችል የአለምንም ፡ ጥበብ ፡ በኔ ፡ ሚያሳፍር ልጁንም ፡ ገለጠው ፡ በእኔው ፡ ሁኔታ እኔን ፡ ውዳቂውን ፡ አከበረ ፡ ጌታ አዝ:- ፀጋው ፡ ነው ፡ እኔን ፡ የሚያቆመኝ ምህረቱ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ የሚያዘምረኝ (፪x) በራሴ ፡ አልቆምኩም ፡ ሚስጥሩ ፡ ገብቶኛል ጸጋን ፡ አትረፍርፎ ፡ እየሱስ ፡ ሰጥቶኛል ከቶ ፡ ዝም ፡ አልልም ፡ አዜምለታለሁ ላከበረኝ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ እሰጣለሁ እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ጌታዬ ፡ ልዩ ፡ ነው የተረሳውን ፡ ሰው ፡ እንዲህ ፡ ሚያስታውሰው አዝ:- ፀጋው ፡ ነው ፡ እኔን ፡ የሚያቆመኝ ምህረቱ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ የሚያዘምረኝ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.