Loading
አበቃለት ፡ ተብሎ ፡ ነበር ፡ ኢየሱሴ ፡ ሲቀበር ወሬ ፡ ሆኖ ፡ ሊቀር አለፈ ፡ ተብሎ ፡ ቢወራ ፡ ነበር ፡ ተብሎ ፡ ሊዘከር ወሬ ፡ ሆኖ ፡ ሊቀር የዓለምን ፡ ታሪክ ፡ ለወጠ ፡ ነገር ፡ ተገለበጠ የአዳም ፡ ዘር ፡ አመለጠ መቃብሩን ፡ ፈነቃቅሎ ፡ ሰይጣንን ፡ ጉድ ፡ አረገ ወደ ፡ አባቱ ፡ አረገ የሰው ፡ኃጢአት ፡ ተወገደ ፡ ተሻረ ፡ የእኛ ፡ አበሳ በትንሳዔው ፡ ድል ፡ ነሳ መቼ ፡ እንደሞተ ፡ ቀረ ፡ ከሙታንም ፡ ተነሳ በትንሳዔው ፡ ድል ፡ ነሳ ኢየሱስ ፡ ተነሳ ጌታዬ ፡ ተነሳ (፪x) ትንሳዔውን ፡ ተናገሩ ፡ የእምነት ፡ አባቶች ፡ መሰከሩ እኔም ፡ ለትውልድ ፡ ልናገርው ኢየሱስ ፡ ተነስቷል ፡ ልመስክረው (፪x) ተነስቷል ፡ ይሄ ፡ ጌታ ማኅተሙን ፡ እርሱ ፡ ፈታ ቅዱሳን ፡ በአንድ ፡ ሁኑና አክብሩት ፡ ከእኔ ፡ ጋራ (፪x) ዕልልታ ፡ ሙገሳ ፡ ሞትን ፡ ድል ፡ ለነሳ ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነስቷል ፡ አክብሩት ፡ ቅዱሳን የታል ፡ ዕልልታ ፡ ለአዳነን ፡ ጌታ የታል ፡ ጭብጨባ ፡ መቅደስ ፡ የሚገባ (፪x) ኃይል ፡ እንደሌለው ፡ ቢመታ ፡ ወደ ፡ መስቀል ፡ ቢነዳ በትንሳዔው ፡ ድል ፡ ነሳ በእንጨት ፡ ላይ ፡ ቢንጠለጠል ፡ ስለ ፡ ሰው ፡ ልጅ ፡ ቢጐዳ በትንሳዔው ፡ ድል ፡ ነሳ ቢያሾፉ ፡ ቢያሳልቁበት ፡ እያሉ ፡ በል ፡ ውረዳ በትንሳዔው ፡ ድል ፡ ነሳ በደሙ ፡ እርቅ ፡ አወረደ ፡ አፈረሰ ፡ ያን ፡ ግድግዳ በትንሳዔው ፡ ድል ፡ ነሳ ኢየሱስ ፡ ተነሳ ፡ ጌታየ ፡ ተነሳ(፪×) ትንሳዔውን ፡ ተናገሩ ፡ የእምነት ፡ አባቶች ፡ መሰከሩ እኔም ፡ ለትውልድ ፡ ልናገርው ኢየሱስ ፡ ተነስቷል ፡ ልመስክረው (፪x) ተነስቷል ፡ ይሄ ፡ ጌታ ማኅተሙን ፡ እርሱ ፡ ፈታ ቅዱሳን ፡ በአንድ ፡ ሁኑና አክብሩት ፡ ከእኔ ፡ ጋራ (፪x) ዕልልታ ፡ ሙገሳ ፡ ሞትን ፡ ድል ፡ ለነሳ ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነስቷል ፡ አክብሩት ፡ ቅዱሳን የታል ፡ ዕልልታ ፡ ለአዳነን ፡ ጌታ የታል ፡ ጭብጨባ ፡ መቅደሱ ፡ የሚገባ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.