Loading
በልዑል መጠጊያ ሁሉን በሚችለው ተማምሬ አድራለሁ ከለላዬ እርሱ ነው እኔ አልፈራም እሱን ይዤው እኔ አልፈራም ተደግፌው ትናንትናን ደርሶ አድኖኝ ዛሬን እንዴት እፈራለሁ የክንዱን የሃይሉን ብርታት በአይኖቼ አይቻለሁ እንዳልፈራ እንዳልሸበር ስሙ ለኔ ዋስ ሆኖኛል የከበረው የጌታ ስም ጠላቶቼን መቶልኛል ለምስኪኑ መታመኛ ለደሃ አደግ የሚራራ ፅኑ አለት ድንቅ ጌታ ኢየሱስ ነው መደገፊያ በአንዳች እንኳን እንዳልፈራ ድንቅ ታምር እየሰራ ህይወቴ ሁሉ እርሱ ገዝቶ አኑሮኛል እየመራ ሸንበቆን አይደለም እኔ የተደገፍኩት ድንገት የሚሰበር መች ሆነ የያዝኩት አስተማማኝ ምርኩዝ ተፈትኖ የፀና የማዕዘኑ ራስ ድጋፌ ነውማ አሃሃ ተደግፌሃለሁ አሃሃ ተማምኜሃለሁ አሃሃ በአስተማማኝ ክንድህ አሃሃ እኔስ አርፌአለሁ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.