Loading
ዝም ፡ ቢል ፡ አንደበት ፡ እጆችም ፡ ባይዘረጉ አይቀንስ ፡ ችሎታው ፡ አይቀንስ ፡ ማዕረጉ የሰማይ ፡ ቅዱሳን ፡ ደግሞም ፡ መላዕክቱ ሁሌ ፡ ይቀኙለታል ፡ ላፍታም ፡ ሳይታክቱ ካፅናፍ ፡ እስካፅናፍ ፡ ተርፏል ፡ የሚያመልከው የፍቅሬን ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ እርሱ ፡ ምን ፡ ሊጎድለው የዳንኩ ፡ እኔ ፡ ያመለጥኩ ፡ እኔ ተፈወስኩ ፡ እኔ ፡ የሞተው ፡ ለእኔ እቀኛለሁኝ ፡ ለመድህኔ (፪x) እዘምራለሁ ፡ ለመድህኔ (፪x) ቢወደድ ፡ አይበዛ ቢፈቀር ፡ አይበዛ ክበር ፡ ቢባል ፡ አይበዛ ቢመሰገን ፡ አይበዛ ነፍሴን ፡ ከሞት ፡ ስለገዛ ክበር ፡ ቢባል ፡ ከቶ ፡ አይበዛ ነፍሴን ፡ ከሞት ፡ ስለገዛ ክበር ፡ ቢባል ፡ ከቶ ፡ አይበዛ አከብርሀለሁ (፬x) እወድሀለሁ (፬x) እንካ ፡ ተቀበለው ፡ አምልኮዬ ፡ ይኸው እንካ ፡ ተቀበለው ፡ ዝማሬየም ፡ ይኸው እንካ ፡ ተቀበለው ፡ ምስጋናዬ ፡ ይኸው እንካ ፡ ተቀበለው ፡ መጓደዴም ፡ ይኸው ዝም ፡ ቢል ፡ አንደበት ፡ እጆችም ፡ ባይዘረጉ አይቀንስ ፡ ችሎታው ፡ አይቀንስ ፡ ማዕረጉ የሰማይ ፡ ቅዱሳን ፡ ደግሞም ፡ መላዕክቱ ሁሌ ፡ ይቀኙለታል ፡ ላፍታም ፡ ሳይታክቱ ካፅናፍ ፡ እስካፅናፍ ፡ ተርፏል ፡ የሚያመልከው የፍቅሬን ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ እሱ ፡ ምን ፡ ሊጎድለው የዳንኩ ፡ እኔ ፡ ያመለጥኩ ፡ እኔ ተፈወስኩ ፡ እኔ ፡ የሞተው ፡ ለእኔ እቀኛለሁኝ ፡ ለመድህኔ (፪x) እዘምራለሁ ፡ ለመድህኔ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.