Loading
አንተ ፡ ስትናገር ፡ (ላለመስማት ፡ ብለን)፪ እንዳንቀበለው ፡ (ምክንያት ፡ ደርድረን)፪ በሃጥያታችን ፡ መጠን ፡ (ልባችን ፡ ከፋና)፪ ለአንተ ፡ እሺ ፡ እንዳይል ፡ (አፈገፈገና)፪ አቤት ፡ መልሰን መልሰን ፡ መልሰን ከሄድንበት ፡ ርቀን(፪) ይገርማል ፡ እሩቅ ፡ ሄደናል ይገርማል ፡ ደጃፍ ፡ ደርሰናል ሳናስቀድምህ፡ ተሸንፈናል(፪) ልባችን ፡ ተሞልቷል ፡ (በዚህች ፡ ዓለም ፡ ነገር)፪ ክፉ ፡ አስገብተናል ፡ (አንተን ፡ አስወጥተን)፪ ለጆሮ ፡ የሚጥሙ ፡ (አሉ ፡ የሚያበሉን)፪ እንደመሻተችን ፡ (የሚያስተምሩን)፪ አቤት ፡ መልሰን መልሰን ፡ መልሰን ከሄድንበት ፡ ርቀን(፪) ይገርማል ፡ እሩቅ ፡ ሄደናል ይገርማል ፡ ደጃፍ ፡ ደርሰናል ሳናስቀድምህ፡ ተሸንፈናል(፪) የበረከት : ብቻ : ሆኗል : ስብከታችን መስቀሉን : መሸከም : አይፈልግ : ስጋችን መንፈስህን : ዘግተን : አስመርረነዋል በምትናገረን : ጆሯችን : ተዘግቷል አቤት ፡ መልሰን መልሰን ፡ መልሰን ከሄድንበት ፡ ርቀን(፪)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.