Loading
ስር ፡ ሳይሰድድብኝ ፡ ህመሜ ፡ ሳይጠና ከሕይወት ፡ ወጥቶ ፡ መሞት ፡ አለና እምቢ ፡ ያለውን ፡ ልቤን ፡ ግራው እዚህም ፡ እዚያም ፡ ይገድላል ፡ በለው ፡ (፪) መልኬ ፡ እየተቀየረብኝ ዛሬ ፡ አንተን ፡ ነገ ፡ ዓለምን ፡ ሆነብኝ ወይ ፡ አልበረድኩኝ ፡ ወይ ፡ አልሞቅኩኝ እንዲያው ፡ መሃል ፡ ላይ ፡ ሆኛለሁኝ መሃል ፡ ሰፋሪ ፡ ሆኛለሁኝ መሃል ፡ ሰፋሪ ፡ ከአፍህ ፡ ይተፋል ፡ (፪) አወይ ፡ ልቤ ፡ ተመለስ ጌታ ፡ ይሻልሃል ፡ የሚወድህ ፡ (፪) ከአፍህ ፡ መተፋት ፡ እጅግ ፡ ያስፈራል ክፉ ፡ ልማዴን ፡ መጣል ፡ ይሻላል እምቢ ፡ ያለውን ፡ ልቤን ፡ ግራው እዚህም ፡ እዚያም ፡ ይገድላል ፡ በለው ፡ (፪) መልኬ ፡ እየተቀየረብኝ ዛሬ ፡ አንተን ፡ ነገ ፡ ዓለምን ፡ ሆነብኝ ወይ ፡ አልበረድኩኝ ፡ ወይ ፡ አልሞቅኩኝ እንዲያው ፡ መሃል ፡ ላይ ፡ ሆኛለሁኝ መሃል ፡ ሰፋሪ ፡ ሆኛለሁኝ መሃል ፡ ሰፋሪ ፡ ከአፍህ ፡ ይተፋል ፡ (፪) አወይ ፡ ልቤ ፡ ተመለስ ጌታ ፡ ይሻልሃል ፡ የሚወድህ ፡ (፪) ልቤስ ፡ አንድ ፡ ነው ፡ ሁለት ፡ ይመኛል ፡ እዚህም ፡ እዚያም ፡ ብሎ ፡ ያስቸግራል እምቢ ፡ ያለውን ፡ ልቤን ፡ ግራው እዚህም ፡ እዚያም/የግብጽ:ሽንኩርት ፡ ይገድላል ፡ በለው ፡ (፪) መልኬ ፡ እየተቀየረብኝ ዛሬ ፡ አንተን ፡ ነገ ፡ ዓለምን ፡ ሆነብኝ ወይ ፡ አልበረድኩኝ ፡ ወይ ፡ አልሞቅኩኝ እንዲያው ፡ መሃል ፡ ላይ ፡ ሆኛለሁኝ መሃል ፡ ሰፋሪ ፡ ሆኛለሁኝ መሃል ፡ ሰፋሪ ፡ ከአፍህ ፡ ይተፋል ፡ (፪) አወይ ፡ ልቤ ፡ ተመለስ ጌታ ፡ ይሻልሃል ፡ የሚወድህ ፡ (፪)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.