Loading
ሰው ፡ ሰው ፡ የሆነበት ፡ የሚኖርበት ፡ ምክንያት ፡ ካልገባው በአካል ፡ ኖረ ፡ እንጂ ፡ የነፍሱን ፡ ክፍተት ፡ በምን ፡ ሊሞላው ኑሮን ፡ ለማሸነፍ ፡ እሮጦ ፡ እሮጦ ፡ ቢደርስ ፡ ከግቡ ተሳካለት ፡ ቢባል ፡ ሃሳቡ ፡ ሞልቶ ፡ እንዲያው ፡ ለደንቡ ግን ፡ ይሄ ፡ አይደለም ፡ የሕይወት ፡ ትርጉሙ ከማግኘት ፡ ይበልጣል ፡ ለተፈለጉበት ፡ መገኘት ፡ በውሉ ሃብትን ፡ ለማካበት ፡ ከመባዘን ፡ ይልቅ ለምን ፡ እንደምንኖር ፡ በተጋን ፡ ለማወቅ አዝ፦ ለምንድነው ፡ የምንኖረው እስትንፋሳችን ፡ የሚቀጥለው ዘመን ፡ ሲጨመር ፡ በእድሜያችን ፡ ላይ ለሰራን ፡ ጌታ ፡ እንድንሰራ ፡ አይደል ፡ ወይ (፪x) እርካታ ፡ በገንዘብ ፡ በመብል ፡ መጠጥ ፡ ከተገደበ በጉብዝናው ፡ ጊዜ ፡ የፈጠረውን ፡ ሰው ፡ ካላሰበ ኋላ ፡ በእድሜው ፡ ምሽት ፡ እንዳይጸጸት ፡ ከአሁኑ ፡ ይንቃ የተፈለገበትን ፡ ምክንያት ፡ ያግኝ ፡ ቀኑ ፡ ሳያበቃ በምድር ፡ ላይ ፡ ያስገኘን ፡ በሰማያት ፡ ያለ አላማ ፡ ሰጥቶናል ፡ የምንኖርብት ፡ ከቁስ ፡ በዘለለ ሁሉም ፡ በየድርሻው ፡ በተሰጠው ፡ ስራ ለመፈጸም ፡ ይሩጥ ፡ የአምላክን ፡ አደራ አዝ፦ ለምንድነው ፡ የምንኖረው እስትንፋሳችን ፡ የሚቀጥለው ዘመን ፡ ሲጨመር ፡ በእድሜያችን ፡ ላይ ለሰራን ፡ ጌታ ፡ እንድንሰራ ፡ አይደል ፡ ወይ (፪x) ሰው ፡ ሰው ፡ የሆነበት ፡ የሚኖርበት ፡ ምክንያት ፡ ካልገባው በአካል ፡ ኖረ ፡ እንጂ ፡ የነፍሱን ፡ ክፍተት ፡ በምን ፡ ሊሞላው ኑሮን ፡ ለማሸነፍ ፡ እሮጦ ፡ እሮጦ ፡ ቢደርስ ፡ ከግቡ ተሳካለት ፡ ቢባል ፡ ሃሳቡ ፡ ሞልቶ ፡ እንዲያው ፡ ለደንቡ ግን ፡ ይሄ ፡ አይደለም ፡ የሕይወት ፡ ትርጉሙ ከማግኘት ፡ ይበልጣል ፡ ለተፈለጉበት ፡ መገኘት ፡ በውሉ ሃብትን ፡ ለማካበት ፡ ከመባዘን ፡ ይልቅ ለምን ፡ እንደምንኖር ፡ በተጋን ፡ ለማወቅ አዝ፦ ለምንድነው ፡ የምንኖረው እስትንፋሳችን ፡ የሚቀጥለው ዘመን ፡ ሲጨመር ፡ በእድሜያችን ፡ ላይ ለሰራን ፡ ጌታ ፡ እንድንሰራ ፡ አይደል ፡ ወይ (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.