Loading
እንዴት ፡ ልፍራ ፡ እንዴት ፡ ልሸበር እግዚአብሔር ፡ ሆኖልኝ ፡ ሞገስ (፪x) አምላካችን ፡ መጠጊያችንና ፡ ኃይላችን ፡ ነህ ባገኘን ፡ በታላቅ ፡ መከራ ፡ ረዳታችን ፡ አሃሃ ፡ ረዳታችን ስለዚህ ፡ ምድር ፡ ብትናወጥ ተራሮች ፡ ወደባሕር ፡ ልብ ፡ ቢወሰዱ እኔ ፡ አልፈራም ፡ አሃሃ ፡ እኔ ፡ አልፈራም ማለፍ ፡ የማይቻለውን ፡ በአንተ ፡ አለፍኩ አስፈሪውን ፡ ጨለማ ፡ ተሻገርኩኝ (፫x) ሁሉን ፡ በአንተ ፡ አለፍኩኝ ክብርህን ፡ ይኸው ፡ አየሁ ፡ ጨለማው ፡ ሰገፈፍ አዲስ ፡ ቀን ፡ ወጣልኝ ፡ ክበር ፡ ያከበርከኝ አምላካችን ፡ መጠጊያችንና ፡ ኃይላችን ፡ ነህ ባገኘን ፡ በታላቅ ፡ መከራ ፡ ረዳታችን ፡ አሃሃ ፡ ረዳታችን ስለዚህ ፡ ምድር ፡ ብትናወጥ ተራሮች ፡ ወደባሕር ፡ ልብ ፡ ቢወሰዱ እኔ ፡ አልፈራም ፡ አሃሃ ፡ እኔ ፡ አልፈራም ለህዝቡ ፡ የሚያዝን ፡ ፍፁም ፡ የሚራራ አማኑኤል ፡ አለ ፡ ዛሬም ፡ ከኛ ፡ ጋራ (፫x) ስናዝን ፡ አፅናንቶን ፡ ኃይልም ፡ ጉልበት ፡ ሰጥቶን መከራችንን ፡ ረሳን ፡ አምላካችን ፡ በእኛ ፡ ከብሮ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.