Loading
አንድ ፡ ፊት ፡ አለ ፡ እኔ ፡ የለመድኩት ማልጄ ፡ ልየው ፡ እንደናፈቅሁት ቀና ፡ ይሆናል ፡ ይሰምራል ፡ ቀኔ የወዳጄን ፡ ፊት ፡ ካየሁት ፡ እኔ (፪x) አዝ፦ በልቶና ፡ ጠጥቶ ፡ መኖር ፡ ሕይወት ፡ እንዳልሆነ ፡ ከገባኝ ፡ ሰንብቶ እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ሚያሰኝ ፡ አንዳች ፡ ነገር ፡ ውስጤ ፡ ገብቶ በልቶና ፡ ጠጥቶ ፡ መኖር ፡ ሕይወት ፡ እንዳልሆነ ፡ ከገባኝ ፡ ሰንብቶ አባቴን ፡ አባቴን ፡ ሚያሰኝ ፡ አንዳች ፡ ነገር ፡ ውስጤ ፡ ገብቶ ሌላውማ ፡ አያምረኝም ፡ እኔ ፡ የኢየሱስ ፡ ነኝ (፪x) እኔ ፡ የኢየሱሴ ፡ ነኝ (፬x) የሕይወት ፡ ብቸኛ ፡ ቁም ፡ ነገር የሆንከው ፡ ወዳጄ ፡ እግዚአብሔር የሆንከው ፡ ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር በህልውናህ ፡ ውስጥ ፡ መኖር መታደል ፡ ነው ፡ ትልቅ ፡ ክብር (፪x) አዝ፦ በልቶና ፡ ጠጥቶ ፡ መኖር ፡ ሕይወት ፡ እንዳልሆነ ፡ ከገባኝ ፡ ሰንብቶ አባቴን ፡ አባቴን ፡ ሚያሰኝ ፡ አንዳች ፡ ነገር ፡ ውስጤ ፡ ገብቶ ሌላውማ ፡ አያምረኝም ፡ እኔ ፡ የኢየሱስ ፡ ነኝ (፪x) እኔ ፡ የኢየሱሴ ፡ ነኝ (፬x) የእኔ ፡ ሞገስ ፡ የእኔ ፡ ተስፋ ነፍሴ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የወደደችው ፡ ጠፋ ነፍሴ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የአፈቀረችው ፡ ጠፋ አንተን ፡ ባየሁበት ፡ ዓይኔ አልታይ ፡ አለኝ ፡ ሌላው ፡ እኔ (፪x) በዚህ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ማጣት ፡ የማልፈልገው ሌላ ፡ ነገር ፡ አይደለም ፡ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ አንተን ፡ ነው (፪x) አዝ፦ በልቶና ፡ ጠጥቶ ፡ መኖር ፡ ሕይወት ፡ እንዳልሆነ ፡ ከገባኝ ፡ ሰንብቶ አባቴን ፡ አባቴን ፡ ሚያሰኝ ፡ አንዳች ፡ ነገር ፡ ውስጤ ፡ ገብቶ ሌላውማ ፡ አያምረኝም ፡ እኔ ፡ የኢየሱስ ፡ ነኝ (፪x) እኔ ፡ የኢየሱሴ ፡ ነኝ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.