Loading
አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ነክቶኛል ፡ ምን ፡ አረጋለሁ እጄን ፡ ዘርግቼ ፡ አመልክሃለሁ (፪x) ምን ፡ አይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ አየቼ ፡ ማላውቀው እግዚአብሔር ፡ ለኔ ፡ በልጁ ፡ የገለጸው በአስደናቂው ፡ ፍቅርህ ፡ የባረካት ፡ ነፍሴ እጀግ ፡ ወዳሃለች ፡ ተመስገን ፡ ኢየሱሴ አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ነክቶኛል ፡ ምን ፡ አረጋለሁ እጄን ፡ ዘርግቼ ፡ አመልክሃለሁ (፪x) የተወደደች ፡ ቀን ፡ አንተን ፡ ያወኩባት እንደምን ፡ ያቺ ፡ ዕለት ፡ የተባረከች ፡ ናት መደነቄ ፡ በዝቷል ፡ ካወኩህ ፡ ጀምሮ ይቆጨኝ ፡ ነበረ ፡ ያንተ ፡ ባልሆን ፡ ኖሮ አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ነክቶኛል ፡ ምን ፡ አረጋለሁ እጄን ፡ ዘርግቼ ፡ አመልክሃለሁ (፪x) በፊትህ ፡ ደስታ ፡ በመገኘትህ ደስ ፡ የምታሰኘኝ ፡ አምላኬ ፡ አንተ ፡ ነህ የፍቅር ፡ ትርጉሙ ፡ የገባኝ ፡ ባንተ ፡ ነው ከማመስገን ፡ በቀር ፡ የምልህ ፡ ምንድን ፡ ነው አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ነክቶኛል ፡ ምን ፡ አረጋለሁ እጄን ፡ ዘርግቼ ፡ አመልክሃለሁ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.