Loading
አዝ፦ በአምላኬ ፡ በስራው ፡ ከምደነቅ ፡ በቀር በቂ ፡ ቃላት ፡ የለኝም ፡ ዘርዝሬ ፡ እንዳልናገር (፪x) ሺህ ፡ ቃላት ፡ ደርድሬ ፡ በሺህ ፡ ቃላት ፡ ባወራው የአምላኬ ፡ ቸርነት ፡ ከዚያም ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ ነው ዝም ፡ ብዬ ፡ ሁሌ ፡ አመሰግናለሁ እርሱ ፡ በሰጠኝ ፡ ፀጋ ፡ መልሼ ፡ አከብረዋለሁ ለአምላኬ ፡ ምሥጋናው ፡ ብዙ ፡ ነው በደስታ ፡ ቆሜ ፡ ላመስግነው የዕልልታው ፡ ድምጽ ፡ በቤቱ ፡ ይሰማ ውዳሴ ፡ ለሆነው ፡ ገናና ፡ ክብርም ፡ ለእርሱ ፡ ነውና ይደርደር ፡ በገናው ፡ ይድመቅ ፡ ዕልልታው ፡ ይሰማ የጌታን ፡ ክብር ፡ ላወራ ፡ ቆሜያለሁ ፡ እኔማ በጐነቱን ፡ እንድናገር ፡ አምላኬ ፡ መርጦኛል ለእርሱ ፡ መለየቴን ፡ ሳስብ ፡ ምሥጋና ፡ ሞልቶኛል ምህረቱ ፡ ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ይቅርታው ፡ ነው ፡ ወደር ፡ የሌለው ያመልካል ፡ ብዙ ፡ የተተወለት ይወዳል ፡ ምህረት ፡ የበዛለት አምላክ ፡ ድንቅ ፡ ያደረገለት ይሰበር ፡ ሽቶ ፡ ብልቃጡ ፡ መዓዛው ፡ ያወደው ከእግሮቹ ፡ ስር ፡ ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ጌታዬን ፡ ላምልከው ግድ ፡ የለም ፡ ዙሪያ ፡ ገባዪ ፡ በእኔ ፡ ግር ፡ ቢለው ምን ፡ ያህል ፡ እንደወደደኝ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው አዝ፦ በአምላኬ/በጌታዬ ፡ በስራው ፡ ከምደነቅ ፡ በቀር በቂ ፡ ቃላት ፡ የለኝም ፡ ዘርዝሬ ፡ እንዳልናገር (፪x) ሺህ ፡ ቃላት ፡ ደርድሬ ፡ በሺ ፡ ቃላት ፡ ባወራው የአምላኬ ፡ ቸርነት ፡ ከዚያም ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ ነው ዝም ፡ ብዬ ፡ ሁሌ ፡ አመሰግናለሁ እርሱ ፡ በሰጠኝ ፡ ፀጋ ፡ መልሼ ፡ አከብረዋለሁ በፍቅሩ ፡ እጆቼን ፡ ይዞኛል አይደክምም ፡ ሁሌ ፡ ይታገሰኛል ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ልበለው መድሃኒት ፡ ለነፍሴ ፡ ፈውስ ፡ ነው ክብር ፡ ታማኝ ፡ ለሆነው ይክበር ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ ውዳሴ ፡ በሠማይ ፡ በምድር ፡ በታላቅ ፡ ዕልልታ እስትንፋስ ፡ ያለው ፡ ይዘምር ፡ ይውጣ ፡ ምሥጋናዉ በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ በላይ ፡ ከብሮ ፡ ጌታ ፡ ለሆነው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.