Loading
Singer
አዝ፦ ዝርግፍ ፡ ጌጤ ፡ ነህ ፡ ኩራቴ ኢየሱሴ ፡ ማዕረጌ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆነ ፡ በአምላኬ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆነ ፡ በአምላኬ (፬x) እንደዐይኖችህ ፡ ብሌን ፡ ተጠንቅቀህልኝ የከበደ ፡ ሸክሜን ፡ ከእኔ ፡ አራግፈህልኝ ቀና ፡ ብዬ ፡ እንድኖር ፡ አንተ ፡ አድርገኸኛል ከክብር ፡ ጋር ፡ ስፍራን ፡ ጌታ ፡ ሰጥተኸኛል የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ ጌታ መመኪያዬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ማረፊያዬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ አዝ፦ ዝርግፍ ፡ ጌጤ ፡ ነህ ፡ ኩራቴ ኢየሱሴ ፡ ማዕረጌ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆነ ፡ በአምላኬ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆነ ፡ በአምላኬ (፬x) እኔ ፡ ያላየሁትን ፡ አንተ ፡ አይተህልኝ የሕይወቴን ፡ ጐዳና ፡ ያቀናናህልኝ ከእኔ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ አንተ ፡ ታስባለህ አላማህ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ያለህ የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ ጌታ መመኪያዬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ማረፊያዬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ አዝ፦ ዝርግፍ ፡ ጌጤ ፡ ነህ ፡ ኩራቴ ኢየሱሴ ፡ ማዕረጌ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆነ ፡ በአምላኬ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆነ ፡ በአምላኬ (፬x) ያሰብከው ፡ ሆነልኝ ፡ አንተ ፡ ለእኔ ፡ ያልከው አንተ ፡ ይሁን ፡ ስትል ፡ ጌታ ፡ ከልካይ ፡ ነው ያሰብከው ፡ ይሆናል ፡ ያየኸው ፡ ይጸናል እንደ ፡ ቃልህ ፡ ሆነህ ፡ ታምነህ ፡ ተገኝተሃል የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ ጌታ መመኪያዬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ማረፊያዬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ (፪x)