Loading
Singer
ከትላንቱ ፡ ዛሬ ፡ ሕይወቴ ፡ አምሮበታል ለቅሶ ፡ ማታ ፡ ነበረ ፡ ጠዋት ፡ ደስታ ፡ ሆኗል ውድቀቴን ፡ ድክመቴን ፡ ለሚፈልገው ሄዳችሁ ፡ ንገሩት ፡ ዛሬም ፡ እንዳለሁ (፪x) ዘንድሮማ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል (፪x) አሁንማ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል (፪x) ለእርሱ ፡ ሲመሽበት ፡ ለኔ ፡ ንጋት ፡ ሆኗል (፫x) ያስለቀሰኝ ፡ ፡ ጠላት ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ አልቅሷል ጨለማዬ ፡ በርቶ ፡ ሁሌ ፡ ያዘምረኛል (፪x) ዘንድሮማ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል (፪x) አሁንማ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል (፪x) ህልምን ፡ አየሁ ፡ ብሎ ፡ ላባቱ ፡ ቢያወራ ወንድሞቹ ፡ ቀንተው ፡ ሸጡት ፡ እንደባሪያ ዘመን ፡ ሲመጣለት ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ሲወጣ ሁሉም ፡ ሰገዱለት ፡ በተራ ፡ በተራ (፪x) ለእርሱ ፡ ሲመሽበት ፡ ለኔ ፡ ንጋት ፡ ሆኗል (፫x) ያስለቀሰኝ ፡ ጠላት ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ አልቅሷል ጨለማዬ ፡ በርቶ ፡ ሁሌ ፡ ያዘምረኛል ዘንድሮማ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል (፪x) አሁንማ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል (፪x) እንዲህ ፡ አልነበረም ፡ ባለፉት ፡ ዘመናት የእኛ ፡ ቤት ፡ ሲፈተሽ ፡ የመከራው ፡ ብዛት የፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ በኢየሱስ ፡ ታድሶ ዛሬም ፡ ይዘመራል ፡ ገደቡ ፡ ተጥሶ (፪x) ዘንድሮማ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል (፪x) አሁንማ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል (፪x) ለእርሱ ፡ ሲመሽበት ፡ ለኔ ፡ ንጋት ፡ ሆኗል (፫x) ያስለቀሰኝ ፡ ጠላት ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ አልቅሷል ጨለማዬ ፡ በርቶ ፡ ሁሌ ፡ ያዘምረኛል