Loading
Singer
Updated 9h ago
ዘምር ፡ ዘምር ፡ ይለኛል ፡ ቀኝህ ፡ ስለደገፈኝ ድቅድቁ ፡ ሌሊት ፡ አለፈ ፡ የሚነጋ ፡ ያልመሰለኝ ባለውለታዬ ፡ ሆይ ፡ ብቸኛ ፡ መመኪያዬ እውነትም ፡ የጭንቅ ፡ ነህ ፡ ልክ ፡ ነበረ ፡ ምርጫዬ ያ ፡ የጨለማ ፡ ዘመን ፡ አለፈ ፡ አበቃ ምርኮ ፡ መጣልኝ ፡ እየጐረፈ ፡ ፡ አበቃ የሀዘን ፡ ሸማ ፡ ከላዬ ፡ ወልቋል ፡ አበቃ ሰላሙ ፡ ልቤን ፡ አጥለቅልቆታል ፡ አበቃ በቃ ፡ ሲለዉ ፡ አበቃ ፡ ገደብን ፡ አበጀዉ ያስጨነቀኝን ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ለወጠዉ ኤፍታህ ፡ ብሎ ፡ ለቆኛል ፡ በደስታ ፡ ልቀኝለት ፡ ይሁን ፡ ያለው ፡ ይሆናል ፡ ተው ፡ ባይ ፡ ከልካይ ፡ የለበት ይብዛልህ ፡ ክብር ፡ ይብዛልህ ፡ ምሥጋና የመኖሬ ምስጢር ጌታ አንተ ነህና ይብዛልህ ክብር ይብዛልህ ምስጋና የመቆሜ ምስጢር ጌታ አንተ ነህና ዞር ፡ ስል ፡ ወደኋላ ፡ ታሪኬ ፡ ሚናገረው ባወራ ፡ የማላፍርበት ፡ ረዳቴ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነዉ ለዚህ ፡ ነዉ ፡ መታመኔ ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ ሚያዘምረኝ በሚያስፈራው ፡ ወጀብ ፡ ላይ ፡ ሰማሁት ፡ አለሁህ ፡ ሲለኝ ከአለት ፡ ንቃቃት ፡ ልውጣ ፡ ከጥሻው ፡ አበቃ በገናን ፡ ላንሳ ፡ ስለውለታው ፡ አበቃ ድምጼ ፡ ይሰማ ፡ በሁሉም ፡ ስፍራ ፡ አበቃ ለሥሙ ፡ ማጠን ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ስራ ፡ አበቃ በቃ ፡ ሲለዉ ፡ አበቃ ፡ ገደብን ፡ አበጀዉ ያሰጨነቀኝን ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ለወጠዉ ኤፍታ ፡ ብሎ ፡ ለቆኛል ፡ በደስታ ፡ ልቀኝለት ፡ ይሁን ፡ ያለው ፡ ይሆናል ፡ ተው ፡ ባይ ፡ ከልካይ ፡ የለበት ፡