Loading
አዝ፦ ዘመኑ ፡ አስፈሪ ፡ ቢሆንም የጌታ ፡ ፀጋ ፡ አላነሰንም ዲያቢሎስ ፡ ቢራቀቅ ፡ ቢመጥቅ ፡ አይተኛም ፡ እኛን ፡ የሚጠብቅ (፪x) እርግጥ ፡ ነው ፡ ጠላታችን ፡ እጅግ ፡ ተራቋል መጠላለፊያውን ፡ ሰውሮ ፡ አስቀምጧል ምድርን ፡ በእጁ ፡ አድርጐ ፡ ይጫወትባታል ለእኛ ፡ ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ እንዳለን ፡ ተረድቷል አዝ፦ ዘመኑ ፡ አስፈሪ ፡ ቢሆንም የጌታ ፡ ፀጋ ፡ አላነሰንም ዲያቢሎስ ፡ ቢራቀቅ ፡ ቢመጥቅ ፡ አይተኛም ፡ እኛን ፡ የሚጠብቅ (፪x) ሃያ ፡ እጥፍ ፡ ቢያነድም ፡ እሳቱን ፡ ሊያስበላን የሚያጠውፋው ፡ ውኃ ፡ ኢየሱስ ፡ አለልን ባህሩን ፡ ቢያሰፋ ፡ ሊያሰምጠን ፡ ወደስር መርከብ ፡ ሆኖ ፡ ማዶ ፡ አለን ፡ የሚያሻግር አዝ፦ ዘመኑ ፡ አስፈሪ ፡ ቢሆንም የጌታ ፡ ፀጋ ፡ አላነሰንም ዲያቢሎስ ፡ ቢራቀቅ ፡ ቢመጥቅ ፡ አይተኛም ፡ እኛን ፡ የሚጠብቅ (፪x) ምድርን ፡ ለቆ ፡ ሰይጣን ፡ በአየር ፡ እየሮጠ ሊያዳክም ፡ የአማኝን ፡ በሩን ፡ ቀጠቀጠ የክርስቲያን ፡ መዝጊያው ፡ አይበገር ፡ ኖሮ መና ፡ ቀረ ፡ ጠላት ፡ ያለ ፡ ኃይሉን ፡ ጥሎ አዝ፦ ዘመኑ ፡ አስፈሪ ፡ ቢሆንም የጌታ ፡ ፀጋ ፡ አላነሰንም ዲያቢሎስ ፡ ቢራቀቅ ፡ ቢመጥቅ ፡ አይተኛም ፡ እኛን ፡ የሚጠብቅ (፪x) ወጥመዱ ፡ በርትቶ ፡ ሊያጠምደን ፡ ቢጣጣር ሕያው ፡ አምላካችን ፡ ይዋጋል ፡ ከእኛ ፡ ጋር የጽዮን ፡ አርበኛ ፡ ቆራጥ ፡ የታጠቀ አንዴም ፡ አልተረታ ፡ አንዴም፡ አልወደቀ አዝ፦ ዘመኑ ፡ አስፈሪ ፡ ቢሆንም የጌታ ፡ ፀጋ ፡ አላነሰንም ዲያቢሎስ ፡ ቢራቀቅ ፡ ቢመጥቅ ፡ አይተኛም ፡ እኛን ፡ የሚጠብቅ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.