Loading
Singer
ዘምን ፡ በዘመን ፡ ሲፈራረቅ ቀኑም ፡ ለቀኑ ፡ ቦታም ፡ ቢለቅ በዓመታት ፡ መሃል ፡ በቀናት ፡ ቁጥር ከፍ ፡ ከፍ ፡ እያልክ ፡ የምትከብር (፪x) የጊዜ ፡ ኃይል ፡ አይለውጥህም አንተ ፡ ህያው ፡ ነህ ፡ አትቀየርም ሚመስልህ ፡ የለም ፡ የሚገዳደርም ማነው ፡ ኃይልህን ፡ የሚከለክልህ (፪x) አዝ:- ፡ ዘመናት ፡ አይለውጡህም ፡ ዓመታት ፡ አይሽሩህም ቀናት ፡ አይቀይሩህም ፡ አንተ ፡ ሁሌ ፡ አንተ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አልፋ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ኦሜጋ ኢየሱስ ፡ ለዘለዓለም ፡ ኢየሱስ ፡ የሚመስልህ ፡ የለም ቢፈራረቁ ፡ ክረምት ፡ ከበጋ አንተ ፡ ግን ፡ ያው ፡ ነህ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ጊዜው ፡ ሲገሰግስ ፡ እንደ ፡ ሰረገላ አንተ ፡ አታረጅም ፡ አትቀርም ፡ ኋላ (፪x) ሁሉ ፡ ፈጥረሃል ፡ በስልጣንህ ተከናወነ ፡ በይሁን ፡ ቃልህ በዙፋንህ ፡ ላይ ፡ ስንት ፡ ነዋሪ አቻ ፡ የለህም ፡ ተወዳዳሪ ፡ ተገዳዳሪ አዝ:- ዘመናት ፡ አይለውጡህም ፡ አመታት ፡ አይሽሩህም ቀናት ፡ አይቀይሩህም ፡ አንተ ፡ ሁሌ ፡ አንተ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አልፋ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ኦሜጋ ኢየሱስ ፡ ለዘለዓለም ፡ ኢየሱስ ፡ የሚመስልህ ፡ የለም (የሚመስልህ ፡ የለም) የጥንቱ ፡ ክንድህ ፡ ይሰራል ፡ ዛሬም ግሩም ፡ ችሎታህ ፡ አልተቀየረም አንተ ፡ አትሻር ፡ አትለወጥም ኢየሱስ ፡ ህያው ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም (፪x) በሙሴ ፡ ዘመን ፡ ባህሩን ፡ ከፍለህ በሐዋርያት ፡ ማዕበሉን ፡ ገሰጽክ ብዙ ፡ ሰርተሃል ፡ በየዘመናት እጅግ ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ ተዓምራት አዝ:- ዘመናት ፡ አይለውጡህም ፡ አመታት ፡ አይሽሩህም ቀናት ፡ አይቀይሩህም ፡ አንተ ፡ ሁሌ ፡ አንተ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አልፋ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ኦሜጋ ኢየሱስ ፡ ለዘለዓለም ፡ ኢየሱስ ፡ የሚመስልህ ፡ የለም (፪x) ዘመናት ፡ አይለውጡህም ፡ አመታት ፡ አይሽሩህም ቀናት ፡ አይቀይሩህም ፡ አንተ ፡ ሁሌ ፡ አንተ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አልፋ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ኦሜጋ ኢየሱስ ፡ ለዘለዓለም ፡ ኢየሱስ ፡ የሚመስልህ ፡ የለም (፬x)