Loading
Singer
Updated 5d ago
ገመዴ ፡ ባማረ ፡ ውብ ፡ ስፍራ ፡ ወደቀችልኝ (፪x) እርስቴም ፡ በእርሱ ፡ በኢየሱሴ ፡ ተዋበችልኝ (፪x) እፎይ ፡ አሰኘኝ ፡ ጌታ ፡ ቤቴ ፡ ገብት መራራ ፡ የሆነውን ፡ ታሪኬን ፡ ለውጦ (፪x) አዝ፦ መጐብኛዬ ፡ ዘመን ፡ መጣ ቀን ፡ ወጣልኝ ፡ በዚህ ፡ ጌታ አርፌያለሁ ፡ በዓለቱ ፡ ላይ ሲደርስልኝ ፡ ጌታ ፡ ከላይ ጌታ ፡ ከላይ ፡ ከላይ (፬x) በምድረበዳ ፡ ውስጥ ፡ ከአለት ፡ ውኃ ፡ አፍልቆ እኔን ፡ አረካልኝ ፡ መገፋቴን ፡ አይቶ የዘመናት ፡ ለቅሶ ፡ እምባ ፡ ታበሰልኝ ልዑል ፡ ከዙፋኑ ፡ ለእኔ ፡ ሲነሳልኝ ምሥጋና ፡ አሄ ፡ ምሥጋና ፡ አሄ ፡ አሄ ምሥጋና ፡ አሄ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ አምልኮ ፡ አሄ ፡ አምልኮ ፡ አሄ ፡ አሄ አምልኮ ፡ አሄ ፡ ለኢየሱስ ፡ ጌታዬ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ (፬x) አዝ፦ መጐብኛዬ ፡ ዘመን ፡ መጣ ቀን ፡ ወጣልኝ ፡ በዚህ ፡ ጌታ አርፌያለሁ ፡ በዓለቱ ፡ ላይ ሲደርስልኝ ፡ ጌታ ፡ ከላይ ጌታ ፡ ከላይ ፡ ከላይ (፬x) መጐብኛዬ ፡ ጊዜው ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል የሃዘኑ ፡ ጊዜ ፡ አልፎ ፡ ደስታ ፡ ቤቴ ፡ ሞልቷል ጠላት ፡ ዐይኑ ፡ እያየ ፡ ይሄው ፡ ጉብኝቴ አከናወነልኝ ፡ ሁሉንም ፡ አባቴ ምሥጋና ፡ አሄ ፡ ምሥጋና ፡ አሄ ፡ አሄ ምሥጋና ፡ አሄ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ዝማሬ ፡ አሄ ፡ ዝማሬ ፡ አሄ ፡ አሄ ዝማሬ ፡ አሄ ፡ ለኢየሱስ ፡ ጌታዬ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ (፮x)