Loading
Singer
ሞቴን ፡ በሕይወት ፡ ቀይሮ ፡ ነገሬን ፡ ሊገለብጥ በጭንቀቴ ፡ ሊያሰፋ ፡ ከፍታን ፡ ለእኔ ፡ ሊሰጥ አዎ ፡ ዘመን ፡ መጣ ፡ ከፊቴ ፡ ፋሬስ ፡ ብዬ ፡ የምጥስበት የያዘኝ ፡ ዳግም ፡ ላይዘኝ ፡ ሰብሬ ፡ የምወጣበት (፪x) ሰባሪው ፡ ጌታ ፡ ከፊቴ ፡ ወጥቷል አማሌቅ ፡ ፈርቶ ፡ መንገዴን ፡ ለቋል ክረምቱ ፡ አልፎ ፡ ጭጋጉ ፡ በኗል ዛሬ ፡ ለእኔ ፡ የዜማ ፡ ጊዜዬ ፡ ሆኗል አምልኮ ፡ ይዤ ፡ ልምጣ ፡ እኔም ፡ በተራዬ ፡ (በተራዬ) (፪x) ሌሊቱን ፡ በሚያነጋው ፡ ታብሷል ፡ እምባዬ ፡ (ታብሷል) (፪x) አምልኮ ፡ ይዤ ፡ ልምጣ ፡ (ይዤ ፡ ልምጣ) ፡ እኔም ፡ በተራዬ (፪x) ቀን ፡ ቀጥሮ ፡ በሚመጣው ፡ (በሚያነጋው) ፡ ታብሷል ፡ እምባዬ (፪x) ከአለት ፡ ንቃቃት ፡ የምወጣበት ፡ እጄን ፡ በአፌ ፡ ላይ ፡ የምጭንበት የጠላቴ ፡ አፍ ፡ የሚዘጋበት ፡ ዘመን ፡ መጣ ፡ የምከብርበት ከእንግዲህ ፡ በቃ ፡ ማልቀስ ፡ በሸለቆ ፡ የናሱም ፡ ደጃፍ ፡ ተበርግዷል ፡ አውቆ ልሂድ ፡ ልውረሰው ፡ ከቶ ፡ አታዘግዩኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ውረሺው ፡ ያለኝ (፪x) እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ውረሺው ፡ ያለኝ (፬x) በቃ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ በጠላቴ ፡ ላይ ፡ ተዘጋ ጌታ ፡ ቀኝ ፡ እጄን ፡ ይዞ ፡ አሻገረን ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ማንኮራኩሩ ፡ ታስሮ ፡ ተጨነቀ ፡ ጠላቴ እኔ ፡ ግን ፡ እየዘመርኩ ፡ ገባሁኝ ፡ ወደርስቴ የማንም ፡ እምባ ፡ ባለዕዳ ፡ አይደለም ፡ ጌታ ዘመናት ፡ ቆጥሮ ፡ ያቆማል ፡ በከፍታ (፪x) ከፍ ፡ ይበል ፡ ጌታ ፡ ማህተሜን ፡ የፈታ (፬x) አምልኮ ፡ ይዤ ፡ ልምጣ ፡ እኔም ፡ በተራዬ ፡ (በተራዬ) (፪x) ሌሊቱን ፡ በሚያነጋው ፡ ታብሷል ፡ እምባዬ ፡ (ታብሷል) (፪x) አምልኮ ፡ ይዤ ፡ ልምጣ ፡ (ይዤ ፡ ልምጣ) ፡ እኔም ፡ በተራዬ (፪x) ቀን ፡ ቀጥሮ ፡ በሚመጣው ፡ (በሚያነጋው) ፡ ታብሷል ፡ እምባዬ (፪x)