Loading
Singer
እግዚአብሔርን ፡ ቆይቼ ፡ ደጅ ፡ ጠናሁት ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ እንደሚሆን ፡ ስላመንኩት እርሱም ፡ ጩኸቴን ፡ ሰምቶ ፡ አዘነልኝ ዘንበል ፡ አለልኝ ፡ ወደኔ ፡ ዘንበል ፡ አለልኝ (፪x) ከረግረጉ ፡ ጭቃ ፡ ከጥፋትም ፡ ጉድጓድ ከአስፈሪው ፡ ጨለማ ፡ ከሰይጣንም ፡ ወጥመድ አስመለጠን ፡ ጌታ ፡ በዛ ፡ ቸርነቱ ምርኮዬም ፡ ተመለሰ ፡ አበራልኝ ፡ ፊቱ አዝ፦ (ቸር ፡ ነው) ፡ ከለመንኩት ፡ በላይ ፡ አብልጦ (ቸር ፡ ነው) ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ አደረገልኝ (ቸር ፡ ነው) ፡ ተትረፈረፈልኝ ፡ ምህረቱ (ቸር ፡ ነው) ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ሆነብኝ ጩኸቴን ፡ ሰማና ፡ አለሁ ፡ አለኝ ፡ ከሞት ፡ አስጣለኝ የማይገባኝን ፡ ክብር ፡ አገኘሁ ፡ ልጁ ፡ ተሰኘሁ በእጆቹ ፡ መዳፍ ፡ ላይ ፡ ቀርጾኛል ፡ ምን ፡ ያስፈራኛል ምህረትና ፡ ቸርነቱ ፡ ይከተሉኛል እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት ፡ እንደሃሳቡም ፡ ለተጠሩት እንደሚናገር ፡ ቅዱስ ፡ ቃሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ፡ ነገር ፡ ሁሉ እግዚአብሔርን ፡ ቆይቼ ፡ ደጅ ፡ ጠናሁት ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ እንደሚሆን ፡ ስላመንኩት እርሱም ፡ ጩኸቴን ፡ ሰምቶ ፡ አዘነልኝ ዘንበል ፡ አለልኝ ፡ ወደኔ ፡ ዘንበል ፡ አለልኝ (፪x) አልቀረም ፡ በከንቱ ፡ ጩኸት ፡ ልመናዬ በጊዜው ፡ መለሰልኝ ፡ ታማኙ ፡ ጌታዬ ውድቀቴን ፡ የሚሹት ፡ አለቀለት ፡ ሲሉ ለበጐ ፡ አደረገልኝ ፡ መከራዬን ፡ ሁሉ አዝ፦ (ቸር ፡ ነው) ፡ ቃልኪዳኑን ፡ ከቶ ፡ የማይረሳ (ቸር ፡ ነው) ፡ የወደቁትን ፡ የሚያነሳ (ቸር ፡ ነው) ፡ ለታመኑት ፡ የማያሳፍር (ቸር ፡ ነው) ፡ ከትቢያ ፡ አንስቶ ፡ የሚያከብር የዘገየ ፡ መስሎ ፡ ሁሌ ፡ ፊት ፡ ይገኛል (፪x) በሞተው ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ ሕይወትን ፡ ይዘራል (፪x) የጸና ፡ ግንብ ፡ ነው ፡ ለአመኑት ፡ የእርሱ ፡ ሥም ፡ የእግዚአብሔር ፡ ሥም ወደርሱ ፡ የሮጠ ፡ አፍሮ ፡ አይመለሥም ፡ ከስሮ ፡ አይመለስም እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት ፡ እንደሃሳቡም ፡ ለተጠሩት እንደሚናገር ፡ ቅዱስ ፡ ቃሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ፡ ነገር ፡ ሁሉ (፪x)